ወ/ሮ ትዕግስት ኪታምቦ ከአባታቸው ከአቶ ኪታምቦ ለማ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ የሺ ደሳለኝ በቀደሞው የሲዳማ አውራጃ በወንዶ ገነት ከተማ ነሐሴ 29/1968 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት የመጀመሪያና 2 ደረጃ ትምህርታቸውን በኦሮሚያ ክልል በአምቦ 1 እና 2 ደረጃ ት/ቤቶች የተከታተሉ ሲሆን ሰኔ 29/1988 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም በመምህርነት በሰርተፊኬት ተመርቀዋል፡፡ ወ/ሮ ትዕግስት በ1998 ዓ/ም በአማርኛ ትምህርት መስክ ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በዲፕሎማ እንዲሁም በተመሳሳይ ትምህርት መስክና ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ነሐሴ 24/2005 ዓ/ም አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ከሰኔ 29/1988 እስከ ግንቦት 30/2001 ዓ/ም በደራሼ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ት/ቤቶች በመምህርነት፣ ከሰኔ 1/2001 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 30/2002 ዓ/ም በደቡብ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት አ/ምንጭ ቅርንጫፍ በሪፖርተርነት እና ከመስከረም 1/2003 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30/2008 ዓ/ም በደራሼ ልዩ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የቋንቋ ጥናትና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ በመሆን ሀገርንና ሕዝብን አገልግለዋል፡፡

ግንቦት 01/2009 ዓ/ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን የተቀላቀሉት ወ/ሮ ትዕግስት በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው በሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት የካምፓስ ሥርዓተ ፆታ አስተባባሪ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በነጭ ሳር ካምፓስ የሥርዓተ-ፆታ ጉዳይ ባለሙያ በመሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ዕለት ድረስ ተቋሙን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ባለትዳርና የ3 ልጆች እናት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ኅዳር 25/2015 ዓ/ም በተወለዱ በ47 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ ትዕግስት ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦችና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት