የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን ነባር የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች፣ እንድሁም ለመልሶ ቅበላ ብቁ ለሆናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ፣ የምዝገባና የትምህርት መጀመሪያ መርሃ ግብር እንደሚከተለው እንዲሆን ወስኗል፡፡
- የመግቢያ ቀን፡ ሰኞ፣ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም.
- የትምህርት ክፍል ምርጫ፡ የ1ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች ሰኞና ማክሰኞ፣ መስከረም 11 እና 12 ቀን 2019 ዓ.ም.
- የምዝገባ ቀን፡ ማክሰኞና ረቡዕ፣ መስከረም 12 እና 13 ቀን 2019 ዓ.ም.
- የትምህርት መጀመሪያ ቀን፡ ሐሙስ፣ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም.
በመሆኑም፣ ሁሉም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች እና ለመልሶ ቅበላ ብቁ የሆናችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሳችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች በአካል በመገኘት የምዝገባ ሂደታችሁን በማጠናቀቅ ትምህርታችሁን በተያዘለት መርሃ ግብር መጀመር እንድትችሉ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ
- ከላይ ከተገለጹት የመግቢያና የምዝገባ ቀናት ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው እንደማያስተናግድ በጥብቅ ያሳውቃል።
- በተጨማሪም፣ በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቀጣይ በይፋ እንደሚገለጽ እናሳውቃለን፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

