በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ የአውቶሞቲቭ ተማሪ የሆነው ዮሐንስ ይኑር በ2016 ዓ/ም የብሩህ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር በማሸነፍ 2,000 የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሥራ ፈጠራና ልማት ማበልጸጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ጀረኔ የብሩህ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር በሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በየዓመቱ እንደሚዘጋጅ ገልጸው ተማሪ ዮሐንስ ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲው አመቻችነት የአፍሪካ-ኤዥያ የወጣቶች ፎረም ላይ ተሳትፎ ልምድ ያገኘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሥራ ፈጠራና ልማት ማበልጸጊያ ማዕከል በኩል የሥልጠና፣ የምክር፣ የድጋፍና የልምድ ልውውጥ ተሞክሮ ሲያገኝ የቆየው ተማሪ ዮሐንስ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል በተካሄዱ የተለያዩ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድሮች ላይ መሳተፉ ሃሳቡን እንዲያበለጽግና የመድረክ አቀራረብ ልምድን እንዲያዳብር ዕድል እንደፈጠረለት ዶ/ር ወንድወሰን አክለዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ በብሩህ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ላይ በመሳተፍና በተከታታይ በማሸነፍ ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት