
- Details
የዩኒቨርሲቲው የተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ከጤና ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት በሚኒስቴሩ አማካኝነት የተደረገን የመድኃኒት ስርጭት ሽፋን ማረጋገጫ ዳሰሳ ጥናት ለማከናወን በአራት ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር ሥራውን ለሚያከናውኑ መረጃ ሰብሳቢዎች ከመስከረም 18-19/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ሥልጠና ማዕከል በተለያዩ ክልሎች የመድኃኒት ስርጭት ሽፋን ማረጋገጫ ዳሰሳ ጥናት ሊያከናውን ነው

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆን ከወዲሁ ይመኛል፡፡
መልካም በዓል!
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ከምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ም/ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በእንቦጭ አረምና በአኩሪ አተር ጠቀሜታ ዙሪያ ከኢንዶኔዥያ በመጡ የመስኩ ባለሙያዎች ለኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች መስከረም 12/2015 ዓ/ም የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በእንቦጭ አረምና በአኩሪ አተር ጥቅሞች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቤልጂየም ሀገር 5 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር የሚሠራው “AMU-IUC – Arba Minch University – Institutional University Cooperation” ፕሮግራም 2ኛ ዙር የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎና በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር ስቴፋን ቲጂስ/Stefaan Thijis/ በተገኙበት መስከረም 11/2015 ዓ/ም በይፋ ተጀምሯል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ