
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ AMU-IUC ፕሮግራም ከGHENT ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አጥቢ እናቶች ከ6 ወር በታች የሆኑ ሕፃናትን የእናት ጡት ወተት ብቻ ማጥባታቸውን ለመለየት የሚያገለግል የምርምር መለኪያ ዘዴ ላይ ከሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ 40 መምህራን ነሐሴ 7/2013 ዓ/ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ነሐሴ 4/2013 ዓ/ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለ 3 መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠ ሲሆን በሌሎች የተለያዩ ጉዳዩችም ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለ3 መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ከኮሌጁ ዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ከጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል እንዲሁም ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት (GIZ) ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ የተፈጥሮ ሀብትና ደን ልማት ባለሙያዎች በ‹‹Geographic Information System(GIS) እና ‹‹Global Positioning System››(GPS) ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከሐምሌ 26 - ነሐሴ 1/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከጋሞ ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ የተፈጥሮ ሀብትና ደን ልማት ባለሙያዎች በ‹‹GIS›› እና ‹‹GPS›› ሶፍትዌሮች ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
በዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት ለሚማሩ 59 የ5ኛ ዓመት የሕግ ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ቦታዎች የሕግ ትምህርታቸውን ተከታትለው የመውጫ ፈተናውን ላላለፉ 87 ተማሪዎች ከሐምሌ 27-30/2013 ዓ/ም የ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና /Exit Exam/ ተሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡