
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአምዩ አዩሲ ፕሮጀክት አማካኝነት የጫሞ ሐይቅ ተፋሰስን መልሶ በማልማትና ሌሎች በፕሮጀክቱ ተግባራዊ እየሆኑ በሚገኙ የማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች ዙሪያ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ሆኔታ ላይ ከጋሞ ዞን፣ ከአርባ ምንጭ እና ከገረሴ ከተማና ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የጫሞ ሐይቅ ተፋሰስን መልሶ ማልማት ዙሪያ በተሰሩ ሥራዎችና ቀጣይ በትብብር መሥራት በሚቻለባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በዋናው ግቢ ያስገነባውን የሕጻናት ማቆያ ማዕከል ሥራ ለማስጀመር የማዕከሉን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት አስመልክቶ ሚያዝያ 7/2017 ለህጻናት ወላጆች ገለጻ (Orientation) ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝትና የኢንደስትሪ ትስስር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የእንስሳት እግርና አፍ በሽታን (Bovine Foot & Mouth Disease) ሥርጭትና መቆጣጠሪያ ዘዴ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው በኮሌጁ የተከናወነ የምርምር ሥራን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ከጋሞ ዞንና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መዋቅር ለተወጣጡ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጂክ ዕቅድ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በተቋቋመ ቡድን ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴርና በሥሩ ከሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ጋር የተፈራረመውን የቁልፍ ተግባራት (KPI) አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የሚያስችል የውስጥ ሱፐርቪዥን ከመጋቢት 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የቆየ የውስጥ ምልከታ ተካሄደ፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የ‹‹KPI›› ትግበራን አስመልክቶ ለአንድ ሳምንት የቆየ የውስጥ ሱፐርቪዥን ተካሄደ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ከጸረ ሙስናና ሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች መልካም ሥነ ምግባር፣ የዲስፕሊን ጥሰቶችና ሊወሰዱ የሚችሉ ቅጣቶችን አስመልክቶ ሚያዝያ 4/2017 ዓ/ም ለዋናው ግቢና ለሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በሥነ ምግባር መመሪያና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ