- Details
የፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን የፌዴራል የመንግሥት ተቋማትን የግዥ ሥርዓት ለማሻሻልና ለማዘመን በ“Electronic Government Procurement /eGP” ዙሪያ ለዘርፉ የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቲዎሪና በተግባር የተደገፈ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ከጳጉሜ 2-4 /2015 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ‹‹Biotechnology›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን ትዕዛዙ መስከረም 04/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዓባያ ካምፓስ በአዲሱ ማኔጅመንት ሕንፃ አዳራሽ ያቀርባል፡፡
- Details
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጃፓን አለምአቀፍ የትስስር ኤጀንሲ (JICA) ጋር በመሆን በግብርና፣ በትምህርት፣በፋይናንስ፣ በዲጂታል አይሲቲና በቱሪዝም ቴክኖሎጂዎች ማኑፋክቸሪንግ እና ማአድን የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማወዳደር ፈጠራቸውን ለማሳደግ የሚረዳቸው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአራት ቀናት አመቻችተዋል፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ‹‹ወደ ዓለም አቀፍ የተመጣጠነ ምግብ ደኅንነት/Towards Global Food and Nutrition Security›› በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የእንሰት ሲምፖዚዬም ከጳጉሜ 1-2/2015 ዓ/ም የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማከናወን ተጠናቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የእንሰት ሲምፖዚዬም በስኬት ተጠናቀቀ
- Details
Arba Minch University in collaboration with Ministry of Agriculture, Bio and Emerging Technology Institute and others co-hosted the First International Enset Symposium: Towards Global Food and Nutrition Security, from September 1-2/2023. Click here to see more photos.
Read more: AMU, MoA & BETin along with others co-hosted the first International Enset Symposium