- Details
ዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ“Water Resource and Irrigation Engineering” ፋካልቲ በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር አበራ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፉን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ አዲሱ አዳራሽ ነሐሴ 26/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
Read more: የዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ የ3ኛ ዲግሪ (PhD) መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ መርሃ ግብር
- Details
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ሲያካሂደው የነበረው ስብሳባ መጠናቀቅ ተከትሎ የስብሳበው ተሳታፊዎች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ የሚገኘውን የእንሰት፣ የጫሞ ሐይቅን መልሶ የማልማት እና ሌሎች የምርምር ግኝት ውጤቶች የመስክ ምልከታ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ2015 ትምህርት ዘመን ሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መርሃ ግብር ከነሐሴ 19-20/2015 ዓ/ም የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝደንቶችና አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝደንቶች በተገኙበት በአርባ ምንጭ ከተማ ኃይሌ ሪዞርት ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በ“AMU-IUC” ፕሮግራምና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በጫሞ ሐይቅ ዳርቻ ረግረጋማ ስፍራ ላይ የምርምር ውጤትን መሠረት በማድረግ እየተከናወነ የሚገኘውን የመልሶ ማልማት ሙከራ /Pilot/ ሥራን ነሐሴ 13/2015 ዓ/ም ጎብኝተዋል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በጫሞ ሐይቅ ዳርቻ እየተከናወነ የሚገኘውን የሙከራ መልሶ ማልማት ሥራን ጎበኙ
- Details
Ministry of Health in collaboration with International Trachoma Initiative organized the Eastern and Southern Africa NTD/Trachoma Cross Boarder Partnership conference with the theme of ‹‹Innovations to accelerate progress towards Elimination›› from August 21-23, 2023, in Arba Minch. Click here to see more pictures.