አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ለፈተና አስፈጻሚዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በአርባ ምንጭ አዞ እርባታ የጉብኝትና ምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጣው ዳርዛ በዩኒቨርሲቲው ስድስቱም ካምፓሶች ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ገልጸው ይህ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ላበረከቱና በትጋት ለሠሩ ፈተና አስፈጻሚዎችና አስተባባሪዎች፣ ለጸጥታና ደኅንነት አካላት እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተቀብሎ ያስፈተናቸው ከ19 ሺህ በላይ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደየመጡበት አካባቢ እየተሸኙ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትን ጨምሮ የአካዳሚክ እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንቶች እንዲሁም ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የፈተና አስፈጻሚዎችና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተገኝተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት