- Details
የዩኒቨርሲቲው የካፒታልና የመደበኛ በጀት አፈፃፀም እየተሻሻለ መምጣቱን የፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማረ ጋማ ገልጸዋል፡፡
ከ2007 በፊት በነበረው አፈፃፀም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር በጀት ተመላሽ ይደረግ የነበረ ሲሆን ከ2005 – 2007 የበጀት ዓመታት የነበረው አፈፃፀም በንፅፅር ሲታይ በ2007 የበጀት ዓመት የመደበኛ በጀት አፈፃፀም 98 በመቶ ሲሆን የካፒታል በጀት ደግሞ 92 በመቶ ነበር፡፡በመሆኑም በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት በድምሩ 10 በመቶ ወይም 37 ሚሊየን ብር ብቻ ፈሰስ ተደርጓል፡፡
በ2008 የበጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው የተመደበው የካፒታልና መደበኛ በጀት 1.2 ቢሊየን ሲሆን ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ አማረ ሁሉም የሥራ ክፍሎች በፋይናንስ ደንብና መመሪያ መሠረት በጀታቸውን 100% መጠቀም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ በተለይም የግዥ ፍላጎቶች በበጀት መዝጊያ ወቅት ተደራርበው በመቅረባቸው ምክንያት ሳይፈፀሙ እንዳይቀሩ የየሥራ ክፍል ኃላፊዎች ክትትል በማድረግ ዕቅዶቻቸውን በወቅቱ አንዲያስፈፅሙ አሳስበዋል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ 46 የበጀትና ፋይናንስ ባለሙያዎችን በማቀፍ በመደበኛና ከመደበኛ የሥራ ሠዓት ውጭ ዘወትር ምሽት እስከ ሁለት ሠዓት እንዲሁም በሳምንት መጨረሻ ቀናት ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
- Details
የኢትዮጵያ የወባ ምርምር ትሥሥር /Malaria Research Network of Ethiopia/ ስድስተኛውን አውደ - ጥናት ከነሐሴ 19-20/ 2007 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካሂዷል፡፡
Read more: ስድስተኛው የኢትዮጵያ የወባ ምርምር ትሥሥር አውደ-ጥናት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
- Details
በኢፌዴሪ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጡት ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰንን አስመልክቶ ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ጋር በመተባበር ለሰው ኃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ሠራተኞች፣ ለሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ጳጉሜ 2/2007 ዓ.ም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የልማትና የሠላም ሥራዎችን ከከተማ አስተዳደሩና ከአካባቢው ኅብረተሰብ ጋር በቅንጅት ለመሥራት የሚያስችለው ‹የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ የአካባቢ አስተዳደርና ማኅበረሰብ ትስስር የሠላም ፎረም› ነሐሴ 08/2007 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተመሥርቷል፡፡
Read more: ‹የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ የአካባቢ አስተዳደርና ማኅበረሰብ ትስስር የሠላም ፎረም› ተመሠረተ