- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በተዘነጉ የሞቃታማ አካባቢ በሽታዎች /Neglected Tropical Diseases/ በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የምርምርና ሥልጠና ማዕከል ማቋቋሙን ነሐሴ 02/2007 ዓ.ም ባካሄደው ወርክሾፕ ይፋ አድርጓል፡፡
Read more: የተዘነጉ የሞቃታማ አካባቢ በሽታዎች የምርምርና ሥልጠና ማዕከል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተቋቋመ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ማዕከል ያደረገው የአርባ ምንጭ ሥነ-ህዝብና ጤና ልማት ፕሮግራም ‹‹ጥራት ያለው መረጃ ለተሻለ ጤና ልማት›› በሚል መሪ ቃል የግማሽ ቀን የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ፡፡
Read more: “የአርባ ምንጭ ሥነ-ህዝብና ጤና ልማት ፕሮግራም ” የባለ ድርሻ አካላት ጉባዔ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በWHaTeR /Water Harvesting Technologies Revisited / ፕሮጀክት በሰገን ህዝቦች ዞን ኮንሶ ወረዳ ያስገነባውን የያንዳ ፋሮ የጎርፍ መስኖ ቅልበሳ ግንባታ ነሐሴ 01/2007 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኮንሶ ወረዳ ያስገነባውን የ ‘ያንዳ ፋሮ ’ የጎርፍ መስኖ ቅልበሳ ፕሮጀክት አስመረቀ
- Details
በዩኒቨርሲቲው የሶስዮሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ ትምህርት ክፍል እና በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ሴቶች ፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ትብብር የህፃናት ህገ-ወጥ ዝውውርና ጉልበት ብዝበዛ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የመጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሐምሌ 9/2007 ዓ.ም ተካሄደ ፡፡ Click here to see the Pictures.
Read more: በህፃናት ህገ-ወጥ ዝውውር እና ጉልበት ብዝበዛ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ተካሄደ
- Details
በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የሒሳብ መምህራንና የድህረ -ምረቃ ተማሪዎች ለሚያደርጉት ጥናትና ምርምር የተሻለ አቅም ለመፍጠርና የሒሳብ ትምህርት በሳይንሱ ዘርፍ ጉልህ ሚና እንዲኖረዉ ለማስቻል <<The Role of Mathematics Now and in the Futuer>>በሚል ርዕስ ሐምሌ 11/2007 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡
በዕለቱ በሳይንስ ትምህርት ላይ ያተኮሩ ሶስት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ስልጠናው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በሒሳብ ትምህርት ለጥሩ ውጤት ለማብቃት የሚያስችሉ የማስተማሪያ ዘዴዎች ፣ የፈተና ዝግጅት እና የጥናታዊ ጽሁፍ ስነ-ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡ በቀጣይም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀትና በመደጋገፍ መስራት እንዳለባቸው በስልጠናዉ ወቅት ተጠቁሟል ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በሒሳብ ትምህርት ዘርፍ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች አናሳ በመሆናቸዉና በሌሎች የሳይንስ ትምህርቶች እየተዋጠ ስለሆነ የትምህርት ክፍሉ ተጠናክሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅና ጥናትና ምርምሮች በመስራት ችግሩን መቅረፍ እንደሚገባው የትምህርት ክፍሉ መ/ር ገብረፃድቅ ግደይ ገልፀዋል ፡፡
በፕሮግራሙ USA ከሚገኘው ሮዋን ዩኒቨርሲቲና ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመጡ የተለያዩ የጥናትና ምርምር አቅራቢዎች፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የሒሳብ ትምህርት ክፍል መምህራን እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዉ የመጡ 110 የድህረ-ምረቃ የክረምት ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡