የአንደኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የሁለተኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ እንዲሁም ሌሎች ሀገራዊና ተቋማዊ አጀንዳዎችን ያካተተ ስልጠና ከመስከረም 7/2008 . ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች እየተሰሠጠ ይገኛል፡፡ የስልጠናዉ ተሳትፎ በፎቶ የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮሮፖሬሽን ዘገባ

Ministry of Education in association with Arba Minch University would be holding comprehensive orientation workshop for the academic staff, administrative personnel, senior and fresh students from September 18, 2015.

በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ቀን ከመስከረም 24-25 ሲሆን ለነባር የዩኒቨርሲቲው ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን መስከረም 19-20 መሆኑን እያሳወቅን በተጠቀሰው ቀን በኣካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እንታደርጉ እንገልፃለን፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለነባር የድህረ-ምረቃ እና የቅድመ- ምረቃ የተከታታይና የርቀት ተማሪዎች ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26-27/2008ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን አዲስ ለሚመደቡ ወይም ለምንቀበላቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ቀን በሌላ ማሰታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

Click here to download the full information.

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር /ቤት

Applied Entrepreneurship Education Program (AEEP), a three-year joint venture of Arba Minch University and Neu-Ulm University of Applied Sciences’ (HNU) completed its second term on Sept. 8, 2015.

የዩኒቨርሲቲው የካፒታልና የመደበኛ በጀት አፈፃፀም እየተሻሻለ መምጣቱን የፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማረ ጋማ ገልጸዋል፡፡
ከ2007 በፊት በነበረው አፈፃፀም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር በጀት ተመላሽ ይደረግ  የነበረ ሲሆን ከ2005 – 2007 የበጀት ዓመታት የነበረው አፈፃፀም በንፅፅር ሲታይ  በ2007 የበጀት ዓመት የመደበኛ በጀት አፈፃፀም 98 በመቶ ሲሆን የካፒታል በጀት ደግሞ 92 በመቶ ነበር፡፡በመሆኑም በበጀት ዓመቱ  ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት በድምሩ 10 በመቶ ወይም 37 ሚሊየን ብር ብቻ ፈሰስ ተደርጓል፡፡
በ2008 የበጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው የተመደበው የካፒታልና መደበኛ በጀት 1.2 ቢሊየን ሲሆን ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ አማረ ሁሉም የሥራ ክፍሎች በፋይናንስ ደንብና መመሪያ መሠረት በጀታቸውን 100%  መጠቀም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ በተለይም የግዥ ፍላጎቶች በበጀት መዝጊያ ወቅት ተደራርበው በመቅረባቸው ምክንያት ሳይፈፀሙ እንዳይቀሩ የየሥራ ክፍል ኃላፊዎች ክትትል በማድረግ ዕቅዶቻቸውን በወቅቱ አንዲያስፈፅሙ አሳስበዋል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ 46 የበጀትና ፋይናንስ ባለሙያዎችን በማቀፍ በመደበኛና ከመደበኛ የሥራ ሠዓት ውጭ ዘወትር ምሽት እስከ ሁለት ሠዓት እንዲሁም በሳምንት መጨረሻ ቀናት ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡