- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያና ደረጃ ዶት ኮም/Dereja.Com/ ከተሰኘ የግል ድርጀት ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2013 እና 2014 ዓ/ም ተመርቀው ሥራ በማፈላለግ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች በሥራ ዝግጁነት /Job Readiness/ ዙሪያ ኅዳር 7/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ሥራ በማፈላለግ ላይ ለሚገኙ የአርባ ምንጭ ከተማ ሥራ አጥ ወጣቶች በሥራ ዝግጁነት/Job Readiness/ ላይ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አማካኝነት በምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርገው የተዘጋጁ 10 ንድፈ-ሃሳቦች ቀርበው ኅዳር 9 እና 12/2015 ዓ/ም ግምገማ ተካሂዶባቸዋል፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስዊዘርላንድ ሀገር ከሚገኘው ኢት-ዙሪች/ETH-Zurich/ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ገጠርንና ከተማን በንጥረ ነገር ዕሴት ሠንሰለት በሚያስተሳስር “RUNRES/ረንረስ” በተሰኘ ፕሮጀክት በአርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያዋ ባሉት የገጠር ቀበሌያት ላይ የተለያዩ ተግባራትን ሲሠራ ቆይቶ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመጠናቀቁ የሥራዎቹን አፈጻጸም እና የፕሮጀክቱን 2ኛ ምዕራፍ ዕቅድና ትግበራ አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ኅዳር 03/2015 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በ“RUNRES/ረንረስ” ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2ኛ ምዕራፍ ዕቅድና የትግበራ አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ
- Details
ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥ ሂደት ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ቢሮዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና እና ሌሎች ተቋማት የምስጋናና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል። ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ትምህርት ሚኒስቴር ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምስጋናና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰጠ
- Details
ቀጠናዊ የኢንዱስትሪ ትስስር ፎረሙ ከአከባቢው ኢንዱስትሪዎችና ቴክ/ሙ/ትም/ሥ/ኮሌጆች በዳሰሳ ጥናት የተገኙ ውጤቶች፣ የ2014 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ጥቅምት 26/2/2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ተወያይቷል፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ቀጠናዊ የእንዱስትሪ ትስስር ፎረም ጉባዔ በአርባ ምንጭ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ተካሄደ

