
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በደቡብ ክልል ከሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች፣ የኦፕሬሽን ክፍል ነርሶች፣ አንስቴዥያ ባለሙያዎችና የሕክምና ዶክተሮች ከግንቦት 19-21/2014 ዓ/ም ‹‹ሰላማዊ የኦፕሬሽን ክፍልና የተሻለ የማገገም ሂደት/Safe Operating Room (OR) and Enhanced Recovery after Surgery Training›› በሚል ርዕስ ሀገር አቀፍ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ‹‹ሰላማዊ የኦፕሬሽን ክፍልና የተሻለ የማገገም ሂደት›› በሚል ርዕስ ሀገራዊ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪነት በማሕፀንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ነጋ ጩፋሞ የተመራ የሕክምና ቡድን በገረሴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመገኘት ለ4 አቅመ ደካማ እናቶች ነፃ የማሕፀን ውልቃት/መንሸራተት ቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት ግንቦት 19/2014 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በገረሴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነፃ የማሕፀን ውልቃት ቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት ተሰጠ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹Christian Aid››/ክርስቲያን ኤይድ/ ከተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር የእንሰት አመራረትና ማብላላት ሂደትን ለማዘመን የሚረዱ በዩኒቨርሲቲው የተፈጠሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ለማዳረስ 3.2 ሚሊየን ብር የተመደበለት ፕሮጀክት በትብብር እየሠሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፕሮጀክቱን የሥራ እንቅስቃሴና አፈፃፀም አስመልክቶ ከድርጅቱ የመጣ ቡድን ግንቦት 16/2014 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ምልከታ አድርጓል፡፡
Read more: የእንሰት አመራረትና ማብላላት ሂደትን ለማዘመን የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ለማዳረስ በትብብር እየተሠራ ነው

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ለጫሞ ካምፓስ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች አቀባበልና የላቀ ውጤት ላመጡ የ3ኛ ዓመት ሴት ተማሪዎች የሽልማት መርሃ ግብር ግንቦት 11/2014 ዓ/ም አካሂዷል፡፡

- Details
ከታኅሣሥ 08/2014 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ምርጫ ግንቦት 14/2014 ዓ/ም አፈ-ጉባኤና ም/አፈ-ጉባኤ በመምረጥ ተጠናቋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ