- Details
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ/ም የ2ኛ ሴሚስተር ትምህርት ለመጀመር ዩኒቨርሲቲው ስለወሰነ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች
- Details
This modest woman Alemwork Gediyhun from Zigm village of Awi Zone in Amhara region is quite diffident to speak about her success. At the face value, she looks shy and it takes time to cajole out her feeling about her achievement; with 3.94 CGPA, she has outclassed all female graduates.
Married at 13, to Mr Bekele Alemayehu, Director of Adisse Primary School in Awi zone has always been encouraging her to study further and had their first girl child after she passed Grade 10. Her father, Mr Gediyhun Bogale and mother Yishamush Getahun wanted her to be a doctor, but she had to be content with Rural Development and Agricultural Extension because of inadequate percentile.
Read more: Think wisely, plan aptly and work hard, says Alemwork
- Details
‹‹የባለድርሻ አካልት ጥምረት ለነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ መልሶ ማገገምና ዘላቂ ጥበቃ›› ጥር 21/2013 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ የትብብርና የድርጊት የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ጥምረቱ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ፣ የፌዴራል የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ የፌዴራል የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች የተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች፣ GIZ Ethiopia፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የግል ባለሀብቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 48 ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ነው፡፡ የባለድርሻ አካላቱን ጥምረት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን በሊቀመንበርነት እንዲሁም ኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን በፀሐፊነት ይመራሉ፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ለመታደግና በዘላቂነት ለማልማት ባለድርሻ አካላት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ጥር 25/2013 ዓ/ም ለካውንስል አባላት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በዕቅድና በአፈፃፀም መካከል ያሉ ልዩነቶችን በማጥበብ፣ በመከለስና ውጤትን መሠረት በማድረግ ማከናወን ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም ባለፉት 6 ወራት ጠንካራ አፈፃፀም ያሳዩ የሥራ ክፍሎችና ግለሰቦች ያላቸውን ቁርጠኝነትና ትጋት እንዲያስቀጥሉና በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በቅድመና ድኅረ-ምረቃ መርሃ-ግብሮች የታዩ ለውጦች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ዶ/ር ዳምጠው አሳስበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ/ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለ3ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን 329 ተማሪዎች ጥር 20/2013 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 111ዱ ሴቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ አስተባባሪና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት የማያልቅና ሁሌም እንደ አዲስ የሚቀጥል ቢሆንም አንድ ደረጃ ላይ ተምሮ መመረቅና ለቀጣይ ሕይወት መዘጋጀት በጣም አስደሳች ነው ብለዋል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለ3ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ