- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲንና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ፈቃዱ ማሴቦ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ዩኒቨርሲቲ ኖርዌይ ከሚገኘው በርጌን ዩኒቨርሲቲ ጋር እየሠራ የሚገኘው የፕሮጀክት ሥራ በመጀመሪያ ዙር አመርቂ ውጤት በማስመዝገቡ ዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ ዙር የʻNorwegian Program for Capacity Development in Higher Education and Research for Development/NORHEDʼ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ሆኗል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የʻNORHEDʼ ፕሮጀክት 2ኛ ዙር ተጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ
- Details
ዩኒቨርሲቲው ለ7ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን 87 የሕክምና ዶክተሮች ታኅሣሥ 24/2013 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 32ቱ ሴቶች ናቸው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ ሀገራችን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሌሎች የሀገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ሁሉ የዩኒቨርሲቲያችን የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የዛሬ ተመራቂ ዶክተሮች ወረርሽኙን ለመከላከል ግንዛቤ በማስጨበጥ እንዲሁም ለኅብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ያለ እረፍት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ሂደት በኮቪድ-19 በሽታ ተይዘው ከዳኑት መካከል መምህራንና ተመራቂ ተማሪዎች ይገኙበታል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ7ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 87 የሕክምና ዶክተሮችን በመጪው ቅዳሜ ታኅሣሥ 24/2013 ዓ/ም በድምቀት ያስመርቃል፡፡ ከተማራቂዎቹ መካከል 32ቱ ሴቶች ሲሆኑ 55ቱ ወንዶች ናቸው፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 87 የሕክምና ዶክተሮችን በመጪው ቅዳሜ ያስመርቃል
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከIBRO እና DANA ፋውንዴሽኖች ጋር በመተባበር የአንጎል ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ለኮሌጁ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም ለመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከታኅሣሥ 12-16/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ የአዕምሮ ጤና ምንነት፣ የአዕምሮ ጤና እድገት እና የአዕምሮ ጤናን የሚጎዱ ሱሶችና አደንዛዥ ዕጾች የሥልጠናው ይዘቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ከጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ባለድርሻ አካላት ጋር የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ አፈፃፀምን ታኅሣሥ 16/2013 ዓ/ም ጎብኝቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ አፈፃፀምን ጎበኘ