- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቪታ/Vita/ ከተሰኘ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት የተሻሻሉና ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በጋሞ ዞን ለሚገኙ ማኅበረሰቦች ለማዳረስ በሚሠራው ፕሮጀክት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ሚያዝያ 28/2014 ዓ/ም ለ5 ዓመታት የሚቆይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ “Vita” ከተሰኘ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ እና ከአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በከተማው ስድስት ቀበሌያት ውስጥ ከሚገኙ 12 ቀጠናዎች ለተወጣጡ 66 አመራሮችና 80 የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች አደረጃጀት አባላት ሚያዝያ 27/2014 ዓ/ም የአመራርነት ክሂሎት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ከተማ የቀበሌ አመራሮችና ለወጣቶች አደረጃጀት የአመራርነት ክሂሎት ሥልጠና ተሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከ‹‹National Institute of Technology›› ጋር በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት ‹‹Application of Novel Techniques for Waste Water Treatment›› በሚል ርዕስ ሚያዝያ 21/2014 ዓ/ም ኦንላይን ሴሚናር አካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
በ2014 የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 1 እና 2 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 3 እና 4 እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ይሆናል፡፡
በመሆኑም ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል በላንቴ ቀበሌ በማኅበር ተደራጅተው ለሚሠሩ፣ የግል ሥራ ፈጥረው ለሚንቀሳቀሱና ሥራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች በመሠረታዊ የሥራ ፈጠራ አመለካከትና ክሂሎት ዙሪያ ሚያዝያ 10/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡