- Details
የዩኒቨርሲቲው የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ለዓባያ፣ ጫሞና ነጭ ሳር ካምፓስ የአስተዳደር ሠራተኞች የጾታና የሥርዓተ ጾታ ምንነት፣ የጾታዊ ጥቃቶች ምንነትና ዓይነቶች፣ ጾታዊ ጥቃቶችን መከላከያ መንገዶች እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ከግንቦት 02-03/2014 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የእግር ኳስ ክሂሎት ላላቸው በአርባ ምንጭ አካባቢ ከሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ማዕከላትና ትምህርት ቤቶች ለተመለመሉ ከ17 ዓመት በታች ለሆኑ 60 ታዳጊዎች ሚያዝያ 28/2014 ዓ/ም የተለያዩ የእግር ኳስ ቁሳቁሶችን አበርክቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ክሂሎት ላላቸው ከአርባ ምንጭና አካባቢው ለተመለመሉ ታዳጊዎች የተለያዩ የእግር ኳስ ቁሳቁሶች አበረከተ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረትና የሰላም ፎረም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር በ2014 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው ለተቀላቀሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከግንቦት 1-2 /2014 ዓ/ም አቀባበል አድርገዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ምቹ የገበያ ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግ በተመሠረተው ዓለም አቀፍ ድርጅት ‹‹Vita›› ስር በኬኒያ ሀገር የተቋቋሙት የ‹‹Dream Team›› አባላት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተቋቋሙት አቻ የ‹‹Dream Team›› አባላት፣ ለግብርና ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ከሚያዝያ 24-26/2014 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹PlantVillage›› እና ‹‹PlantVillageNuru›› ሶፍትዌር መተግበሪያ (Software Application) አጠቃቀም ዙሪያ በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል በሥራ ፈጠራ አመለካከትና በመሠረታዊ የሥራ ፈጠራ ክሂሎት ዙሪያ ሚያዝያ 29/2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ለዓባያ፣ ጫሞ፣ ኩልፎ፣ ነጭ ሳርና ዋናው ግቢ ተመራቂ ተማሪዎች ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የሥራ ፈጠራ ማበልጸጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ጀረኔ ሥልጠናው ለተመራቂ ተማሪዎች በሥራ ፈጠራ ክሂሎት ላይ በቂ ግንዛቤ በማስጨበጥ ተመራቂዎች የተለያዩ አማራጮችን ተመልክተው ራሳቸውንና ሌሎችን መጥቀም የሚያስችል አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡
ራስን ማወቅ ለሥራ ፈጠራ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ያሉት አሠልጣኝ መ/ርት አስቴር ሰይፉ ሥልጠናው ተማሪዎቹ ለሥራ ፈጠራ፣ ለራሳቸው እና ለሌላው ሰው ያላቸው አመለካከት መልካም አንዲሆን በማድረግ ተቀጣሪ ሳይሆኑ ቀጣሪ በመሆን ለቀጣይ ትውልድ የሥራ ፈጠራ እድልን እንዲያመቻቹ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሠልጣኝ መ/ር አሰግድ አጥናፉ በበኩላቸው ሠልጣኞች የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ፣ እችላለሁ የሚለውን ስሜት አዳብረው በመነቃቃት ወደ ሥራ እንዲገቡና ውጤታማ እንዲሆኑ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ የጊዜና የሀብት አጠቃቀም፣ የዕቅድ አዘገጃጀትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤን በመፍጠር ተማሪዎቹ ዕውቀት እንዲጨብጡ መደረጉን አሠልጣኙ አብራርተዋል፡፡
ሠልጣኝ ተማሪዎች ከሥልጠናው ያገኘነው ዕውቀት ለቀጣይ ሥራችን አጋዥና ለሥራ በር የሚከፍትልን በመሆኑ ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ እንዲሁም ሥራ በመፈለግ ጊዜያችንን ከማጥፋት የሚታደገን ነው ብለዋል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት