
- Details
በ"AMU-IUC" ፕሮግራም 2ኛ ዙር ቤልጂየም ሀገር በሚገኙ 5 ዩኒቨርሲቲዎች የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ላገኙ ተማሪዎች የትውውቅና የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ጥር 5/2015 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በ"AMU-IUC" ፕሮግራም 2ኛ ዙር የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ላገኙ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተካሄደ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም እየጠፋ ያለውን የኦንጎታ ቋንቋ ለመታደግ በቋንቋው ላይ የምርምር ጥናት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ጥር 7/2015 ዓ/ም ጂንካ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ኦሞ ምርምር ማእከል ውስጥ አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ ኃይሉ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፉን የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት ጥር 03/2015 ዓ.ም አቅርቧል፡፡
ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ ያቀረበው የመመረቂያ ጽሑፍ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአየር ንብረት ለውጥ፣ በምግብ ዋስትናና በገጠር አኗኗር መተዳደሪያ ዕቅድ ዙሪያ “Climate Variability, Smallholder Rural Households’ Economic Base and Food Security Status in North Shewa, Oromia Region, Ethiopia” በሚል ርዕስ ላይ የተከናወነ ነው፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
ከጋሞ እና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ከደራሼና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ 30 የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሴቶች ሊግ መካከለኛ ሴት አመራሮች የአመራርነትንና የተግባቦት ክሂሎትን ለማሳደግ የሚያስችል ሥልጠና ከጥር 3-4/2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ አመራር ዝግጅት ምልመላና ስምሪት ሥርዓት ማስተግበሪያ መመሪያ መሠረት በዩኒቨርሲቲው ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ቦታ በተደረገው ግልጽ ውድድር መሠረት የዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ከታኅሣሥ 22/2015 ዓ/ም ጀምሮ ዶ/ር ቦጋለ ገብረማርያም የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ የኃላፊነት ሹመት ሰጥቷል፡፡
Read more: ዶ/ር ቦጋለ ገብረማርያም የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ