
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ጾታዊ ጥቃትንና ትንኮሳን መከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ ከዋናው ግቢና ከተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የሴት ተማሪዎች ኅብረት አደረጃጀቶች ጋር ከኅዳር 30-ታኅሣሥ 01/2015 ዓ/ም በየካምፓሶቻቸው ውይይት አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹GIZ››፣ እፉዬ ገላ ኢቨንት ቴክኖሎጂና ኮንሰልተንሲ እና ኢትዮጆብስ ጋር በመተባበር ከኅዳር 22-26/2015 ዓ/ም በጫሞ ሐይቅ ዙሪያ ሀካቶን አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የእግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከደቡብ ክልል ለተወጣጡ በሥራ ላይ ያሉ አሠልጣኞች ከኅዳር 20 - 29/2015 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ‹‹CAF D License›› የእግር ኳስ አሠልጣኝነት ሥልጠና ተጠናቋል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው ሲሰጥ የነበረው የእግር ኳስ አሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

- Details
የዩኒቨርሲቲው አመራር አካላትና መምህራን በቀን 01/4/2015 ዓ/ም ሰፊ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ከሰኞ (ታኅሣሥ 03/2015 ዓ/ም) ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራውን በተሟላ ደረጃ ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በመሆኑም ሁሉም መምህራን እና ተማሪዎች በትምህርት ክፍለ ጊዜያችሁ መሠረት በመማር ማስተማር ሥራው ላይ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ከአደራ ጭምር ይገልጻል፡፡

- Details
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የተከበረው ዓለም ዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ9ኛ ጊዜ ‹‹ሙስናን መታገል በተግባር!›› በሚል መሪ ቃል ከኅዳር 26-27/2015 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ በፕሮግራሙም የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ግቢ ከማጽዳት ጀምሮ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር፣ ዕለቱን አስመልክቶ የተለያዩ ሰነዶች፣ ግጥሞችና መነባንቦች ቀርበዋል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ