- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በጎፋና ኮንሶ ዞኖች እና በደራሼ ልዩ ወረዳ በዝናብ እጥረት በተከሰተ ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 2.1 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የምግብ እህል ድጋፍ ከታኅሣሥ 26-28/2015 ዓ/ም በየሥፍራዎቹ በመገኘት አስረክቧል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል በ‹‹ Disaster Risk Management›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ ኃይሉ ሐሙስ ጥር 04/2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የመመረቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናዉ ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀርባል፡፡
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ ት/ክፍል በ ‹‹Development Economics›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ኤዞ ኤማኮ ማክሰኞ ታኅሣሥ 25/2015 ዓ/ም የምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
‹‹በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ሚና›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ካውንስል እና መምህራንና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ከታኅሣሥ 24-27/2015 ዓ/ም የሚቆይ ሀገራዊ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ‹‹በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ሚና›› በሚል መሪ ቃል የመምህራንና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ውይይት እንደቀጠለ ነው
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ‹‹iCog Anyone Can Code›› ከተሰኘ ድርጅት፣ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከሁዋዌ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ካሉ ልማት፣ ጫሞ፣ ዓባያና አርባ ምንጭ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ከታኅሣሥ 20 - ጥር 5/2015 ዓ/ም የሚቆይ ዲጂትረክ/ DigiTruck/ በተሰኘ ፕሮጀክት የአይ ሲ ቲ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በዲጂትረክ/DigiTruck/ ፕሮጀክት በአይ ሲ ቲ/ICT/ ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

