
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 24/2014 ዓ/ም በተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ የመንግሥት ምሥረታ ክቡር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ የተሰማውን ደስታ እየገለጸ የኃላፊነትዎ ዘመን የኢትዮጵያ ብልፅግና የሚረጋገጥበት፣ የከፍታና የስኬት እንዲሆን በመላው የዩኒቨርሲቲው መኅበረሰብ ስም የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲሱን የመንግሥት ምሥረታ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፈ

- Details
የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ት/ክፍል ጋር በመተባበር በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ መስከረም 20/2014 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ
Read more: በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ለማስጀመር የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ ተካሄደ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን 5 ሺህ ያህል ተማሪዎች በ3ኛ፣ በ2ኛ እና በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ-ግብሮች መስከረም 29/2014 ዓ.ም በዓባያ ካምፓስ ስቴዲዬም ለ34ኛ ዙር እንዲሁም የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎችን መስከረም 30/2014 ዓ.ም በሳውላ ካምፓስ ለ4ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን 5 ሺህ ያህል ተማሪዎችን ሊያስመርቅ ነው
- Details
የ4ኛ ዓመት የኤሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ምኅንድስና ተማሪዎች ከ2014 ዓ/ም ተመራቂ ባቾች ጋር እኩል እንዲመረቁ ለማድረግ ከሌሎቹ ተማሪዎች ቀድመው ወደ ኢንስቲትዩቱ በመግባት የ2ኛ ሴሚስተር ትምህርታቸውን በመጨረስ ለኢንተርንሺፕ እንዲወጡ ይቻል ዘንድ የፋከልቲው ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ መስከረም 30/2014 ዓ/ም ወደ ካምፓስ እንድትገቡና ከሰኞ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

- Details
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የ2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዙር የምርምር ንድፈ ሃሳብ ግምገማ መስከረም 14/2014 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ/ም የምርምር ንድፈ ሃሳብ ተገመገመ