• SMIS
  • AMU Mail
  • Digital Library
  • AMU RDB
  • E-learning
  • AMU
    • About AMU
    • Presidents Message
    • Campus Guide
    • Contact us
  • Administration
    • Presidents' Office
      • AMU President
      • Academic Affairs
      • Research and Community Service
      • Administration
  • Directorates
  • Academics
    • School of Graduate Studies
    • Institutes
      • Arba Minch Institute of Technology
      • Arba Minch Water Technology
    • Colleges
      • Agriculture
      • Business & Economics
      • Medicine and Health Sciences
      • Natural & Computational Sciences
      • Social Sciences & Humanities
      • Continuing & Distance Education
      • Sawla Campus
    • Schools
      • School of Law
      • School of Pedagogical and Behavioral Sciences
      • School of Medicine
    • Sport Academy
  • Research
  • Registrar
    • About Us
    • Alumni Registration
    • Alumni
  • Partnership
    • Our Partners
      • International Partners
      • Local Partners
    • Ongoing Projects
    • Completed Projectss
      • Recently Completed
      • Past Projects
    • GCPM Online Forms
  • Journals
    • OMOIJS Journal
    • EJBSS Journal
    • EJWST Journal
    • AMUJCLS Journal
    • EIJET journal
  • Symposia
    • Enset Symposium
    • Enset Symposium 2024

15ኛው ዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ሲምፖዚዬም ተካሄደ

Details
Thu, 23 July 2015 11:19 am

በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምር ዳይሬክቶሬትና በውሃ ሀብት ምርምር ማዕከል ዳይሬክቶሬት ትብብር 15ኛው ዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ሲምፖዚዬም ከሰኔ 26 እስከ 27/2007 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡

ሲምፖዚዬሙ በዘላቂ የውሃ ሃብት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት የጋራ መድረክ በመፍጠር የምርምር ውጤቶችን እንዲያቀርቡና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ ለማድረግ ያለመ መሆኑን በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንሲትቲዩት የውሃ ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር መኮንን አያና ተናግረዋል፡፡ ለአገር ልማት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤቶች የሚቀርቡበት መድረክ በመሆኑ በውሃ ሃብት ዙሪያ ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት ሊሆን የሚችል መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ በመክፈቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያ በውሃ ሀብት ያላትን ከፍተኛ አቅም በአግባቡ ለመጠቀም እንዳትችል በመስኩ የሚታየው የባለሙያና የፋይናንስ አቅም ውስንነት ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል፡፡የውሃ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም በሳይንሳዊ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መደገፍ እንደሚገባው የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲው በግንባር ቀደምነት ባለሙያዎችን በማሰልጠን በዘርፉ የሚታየውን ውስንነት ለመቅረፍ የራሱን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የምርምር ዳይሬክተር አቶ አቢቲ ጌታነህ በመስኖ ልማት ፕሮጀክት፣በሰው ኃይል ስልጠና፣ በምርምር እና በሌሎችም ተያያዥ ዘርፎች በሚኒስቴር መ/ቤቱ በኩል የታቀዱ ሥራዎችንና የዩኒቨርሲቲዎችን ሚና አስመልክተው ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በመስኖ ልማት ሀገራችን ካላት አቅም ከ40-50 በመቶ መጠቀም የተቻለ ሲሆን በኤሌክትሪክ ኃይል ከውሃ ፣ ከነፋስና ከጂኦተርማል ኃይል እንዳላት ከሚገመተው 45 ሺ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም 10ሺ የሚሆነውን ለማሳካት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በዘርፉ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት በማፍራትና በጥናትና ምርምር የተሻለ ሥራ እንደሚሠሩ ጠቁመዋል፡፡

በሲምፖዚዬሙ ከተለያዩ ተቋማት በመጡ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች 62 የጥናትና ምርምር ጽሑፎች ተመርጠው 28ቱ በመድረክና 11 ጥናቶች በፖስተር ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም ኔዘርላንድ ከሚገኘው ዋግናይን ዩኒቨርሲቲ የመጡትና በውሃ ሃብት ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ፕሮፌሰር ሄንክ ሪትማን ‹‹በፍሳሽ አወጋገድ ዙሪያ የተዘነጉ እውነታዎች ›› በሚል ርዕስ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ የፍሳሽ አወጋገድ ምንነት፣ ዓላማና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ዳሷል፡፡

በሲምፖዚዬሙ የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ከውሃ ሀብት ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችና አጋር ተቋማት በአጠቃላይ 120 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በማጠቃለያው የጥናትና ምርምር ጽሑፍ ላቀረቡ ባለሙያዎችና ለሲምፖዚዬሙ ስኬት ጉልህ ድርሻ ለነበራቸው አካላት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገ/ም/ፕሬዝዳንት አማካኝነት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡



በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ማላመድና ሽግግር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

Details
Thu, 23 July 2015 11:18 am

የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያና ኮሜርሻላይዜሽን ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ማላመድና ሽግግር ዙሪያ ከግንቦት 27-28/07 ዓ/ም የሁለት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ሥልጠናው ለዩኒቨርሲቲውና ለአካባቢው ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ማላመድና ሽግግር እንዲሁም በአእምሯዊ ንብረት አጠባበቅ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ መሆኑን የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደሴ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ሀብት ጽ/ቤት ባለሙያ አቶ ፈቃዱ ኃይሌ በስልጠናው ላይ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መ/ቤቱ በህብረተሰቡ ዘንድ የአእምሯዊ ንብረት እውቀት እንዲዳብርና በቂ የህግ ጥበቃ እንዲያገኝ በመሥራት ላይ ነው፡፡

አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠር፣ የማላመድና የማሸጋገር ሥራዎችን በማጠናከር ለማህበረሰቡ ችግር አማራጭ መፍትሄ ለመስጠት በሚቻልበት ሂደትና የፈጠራው ባለቤቶች ከውጤቱ መጠቀም እንዲችሉ እየሰራ መሆኑን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ አቶ ተረፈ ቤኛ ገልፀዋል፡፡ ይህም በሚኒስቴር መ/ቤቱ ሀገራዊ አቅጣጫዎችን በተከተለ መንገድ ልማቱን የሚያፋጥኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ወደ ተግባር እንዲለወጡ የማድረግ ሥራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኙም ነው አቶ ተረፈ የተናገሩት፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ ሥራዎችን በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ማላመድና ሽግግር ላይ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ከዚህም ጎን ለጎን በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፎች ላይ የተደራጁና መሰል ሥራዎችን በማከናወን ላይ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን አቅም ከማጎልበት አንጻር የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር ግብዓት የሚሆን ስልጠና ለማዘጋጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር ጉቼ ተናግረዋል ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የማህ/አገ/ዳ/ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኮሜርሻላይዜሽን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከሚሰሩ አዳዲስ የምርምር ሥራዎች ውስጥ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙትን በመምረጥ፣ በመገምገምና ወደ ተግባር እንዲለወጡ በማበረታታት ተቀባይነት ያገኙትን በኢትዮጵያ አእምሯዊ ሀብት ጽ/ቤት ዕውቅና እንዲሰጣቸው ያመቻቻል፡፡

በሥልጠናው በአርባ ምንጭ ከተማ ከተደራጁ ጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት፣ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችና በዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተወጣጡ መምህራንና ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማላመድና የማሸጋገር ሥራዎችን በትብብር እንደሚሰራ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አለማዬሁ ታዬ ገልፀዋል፡፡

በወቅታዊ የሲቪል ምህንድስና ሥራ ልምዶች ላይ ያተኮረ ሲምፖዚዬም ተካሄደ

Details
Thu, 23 July 2015 11:16 am

በኢትዮጵያ የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር ድጋፍ በዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በወቅታዊ የሲቪል ምህንድስና ሥራ ልምዶች ላይ ያተኮረ ሲምፖዚዬም ግንቦት 4/2006 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ በሲምፖዚዬሙ ከሲቪል ምህንድስና ጋር የተያያዙ ሙያዊ ጉዳዮችን በሚመለከት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተርና የእለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ እንደገለጹት በአገራችን በምህንድስናው መስክ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተጽዕኖዎች መጎልበት በመቻላቸው የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ከማደጉም አልፎ ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ስኬት የበኩሉን በመወጣት ላይ ነው፡፡ ኢንደስትሪው በግልም ሆነ በመንግሰት የሚጠይቀው የሰው ኃይል በእጅጉ በመጨመሩ በዘርፉ በእውቀትና በክህሎት የዳበሩ ባለሙያዎችን ማፍራት ወሳኝ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ይህን መሰል ፎረሞች መዘጋጀታቸው ሙያዊ አቅምን ለማሳደግና እርስ በእርስ ለመማማር እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

የአገሪቱ የልማት ህዳሴ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረጉ ረገድ በሲቪል ምህንድስና የሙያ መስክ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች ሚና የጎላ በመሆኑ ማህበሩ ይህን ለመደገፍና አቅማቸው እንዲጎለብት ለማድረግ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሲምፖዚዬሙ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ በቴክኖሎጂ ኢንሲትቲዩት የሚገኙ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም የሲቪል ምህንድስና የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ150 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር በ2004 ዓ/ም ህጋዊ እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ሲሆን የዘርፉ ተማሪዎች ከሙያው የሚጠበቀውን ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ በታማኝነትና በጥሩ ስነ-ምግባር የታነፁ እንዲሁም የበቁ ምሁራንን በማፍራት ያደገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚያስችል ራዕይን አንግቦ የሚንቀሳቀስ ማህበር ነው፡፡

ለዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተሰጠ

Details
Thu, 23 July 2015 11:16 am

የሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ለ20 የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራንና ረዳት የቴክኒክ ባለሙያዎች ከግንቦት 7 እስከ 9/2007 ዓ/ም በህይወት ክህሎትና አመራር ሰጪነት ሚና ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በሥነ-ልቦና እና በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህራን የተሰጠው ሥልጠና ዓላማ የመምህራኑን በራስ መተማመን በማጎልበት የችግር ፈችነትና ውሳኔ ሰጪነት ሚናቸው ከፍ እንዲል ማገዝ መሆኑን በዩኒቨርሲቲው የስርዓተ-ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ሙኒት መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

በሀገራችን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴት መምህራን ቁጥርና በኃላፊነት ደረጃ ያላቸው ተሳትፎ እያደገ ቢሆንም የሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመድረሱን ያወሱት ዳይሬክተሯ ለዚህም ሴቶች ከተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ተፅዕኖዎች ሙሉ በሙሉ አለመላቀቃቸው እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡

የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል እነዚህን ተጽዕኖዎችንና እንቅፋቶችን በመቅረፍ በራስ መተማመናቸውን እንዲጨምሩና የውሳኔ ሰጪነት ሚናቸውን እንዲያጎለብቱ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ የዩኒቨርሲቲውን የአስተዳደር ዘርፍ ሴት ሠራተኞች እንዲሁም ሴት መምህራንና ተማሪዎችን ለመደገፍ እቅድ አዘጋጅቶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ለውጥ ያመጣሉ ተብለው በሚታሰቡ ጉዳዮች ባለሙያዎችን በመጋበዝ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችንና ሌሎች ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛ አመት ክብረ በአል በድምቀት ተከበረ

Details
Thu, 23 July 2015 11:10 am

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን አራተኛ አመትና የግንባታውን መጋመስ በማስመልከት መጋቢት 29/2007 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው ዕለቱን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡

የግድቡ ግንባታ ኃይል ከማመንጨት ዓብይ ዓላማው ባሻገር ተምሳሌታዊ የሆነ ጠቀሜታ ያለውና የአይቻልም መንፈስን ሰብሮ ወደ ይቻላል መንፈስ ያሸጋገረ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ ገልፀዋል፡፡ እየተካሄደ ላለው የልማትና የዲሞክራሲ ሂደት በተለይም ለኢንዱስትሪው ሴክተር በቂ ኃይል በማቅረብ ልማታችንን የሚያፋጥን መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት ለመውጣት እያሳየ ያለውን ጥረት ለማስቀጠል የህዳሴ ግድቡን ጨምሮ የተጀመሩ ልማቶችን ከግብ ለማድረስ ሁሉም ዜጋ በቁርጠኝነት መረባረብ አለበት ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ በቀለ አስገንዝበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ የአገራችንን የውሃ ኃብት ለማበልፀግ ታስቦ የተቋቋመ እንደመሆኑ በዘርፉ የሠለጠኑ ምሁራንን ለአገር በማበርከት ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንደሚጠበቅበት እሙን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተቋሙ ሠራተኞች የሁለት ወር ደመወዛቸውን መቶ ፐርሰንት በመክፈል ቦንድ የገዙ ሲሆን ተማሪዎችም ከወር ቀለባቸው በመቀነስ ለግንባታው ስኬት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

‹‹አሻራችን ያረፈበት ነውና ኩራት ሊሰማን ይገባል!›› ያሉት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ነገ የተሻለች ሀገር እንድትኖረን ለማድረግ ሁሉም ዜጋ ለግድቡ ግንባታ ካለው ላይ በመቀነስ የሚደያደርገውን ድጋፍ ሳያቋርጥ መቀጠል አለበት በማለት አሳስበዋል፡፡

ፕሮግራሙ በተለያዩ የስነ-ጹሁፍ ስራዎች፣መዝሙሮች፣ስፖርታዊ ውድድሮችና በሌሎች አዝናኝ ትዕይንቶች ደምቆ የተከበረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣የአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

  1. ለዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሜይንስትሪሚንግ ላይ ስልጠና ተሰጠ
  2. “ምርምር ለልማት” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር አውደ ጥናት ተካሄደ
  3. የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የ‘ISIS’ን የሽብር ጥቃት በጥብቅ አወገዘ
  4. ዩኒቨርሲቲ አቀፍ የትምህርት ጥራትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ማጎልበቻ ፎረም ውይይት ተካሄደ፡፡

Page 460 of 524

  • 455
  • 456
  • 457
  • 458
  • 459
  • 460
  • 461
  • 462
  • 463
  • 464

Downloads

  • Newsletter
  • Registrar
  • Academic Calendar
  • Finance & Budget Transparency

Quick Links

  • News
  • Vacancies
  • AMU Intranet
  • ICT Center

Systems

  • SMIS
  • AMU Mail
  • Digital Library
  • AMU RDB
  • E-learning
  • Facebook
  • X
  • Telegram
  • Youtube
  • Email

Contact us

Corporate Communication
P.O. Box 21
Arba Minch University

Tel: +251-46881-4986
Fax: +251-46881-0820/0279
E-mail: corcom@amu.edu.et , ictc@amu.edu.et

Registrar

  • About Us
  • Alumni
  • Alumni Registration
  • Contact us

Colleges

  • Agriculture
  • Business & Economics
  • Medicine and Health Sciences
  • Natural Sciences
  • Social Sciences & Humanities

Systems

  • SMIS
  • AMU Mail
  • Digital Library
  • AMU RDB
  • E-learning

Copyright © 2025 Arba Minch University. 

  • Campus Guide
  • Contact Us
  • Sitemap