
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ትራንስፎርሚንግ አግሪካልቸር(ETA) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የእንሰት አመራረት ሂደትን የሚያሻሽሉ ዘመናዊ ማሽኖችን በማባዛት ለማኅበረሰቡ በስፋት በማዳረስ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከግል ቴክኖሎጂ አምራች ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት ነሐሴ 23/2015 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የእንሰት አመራረት ሂደትን የሚያሻሻሉ ዘመናዊ ማሽኖችን በማባዛት ለማኅበረሰቡ በስፋት ለማዳረስ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹International Bamboo and Rattan Organization/INBAR›› ከተሰኘና መቀመጫውን ቻይና ካደረገ ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የቆላ ቀርከሃ ችግኝ በማፍላት የዩኒቨርሲቲው፣ የድርጅቱ፣ የክልሉና የዞኑ አመራሮች በተገኙበት በላንቴ ኦቾሎ ቀበሌ ነሐሴ 25/2015 ዓ/ም የተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ ድርጅቱ ከሰጠው አንድ ኪሎ የቀርከሃ ዘር ውስጥ 15 ሺህ የሚሆኑትን ማፍላት የተቻለ ሲሆን በዕለቱ ስድስት በመቶ የሚሆኑት ችግኞች በላንቴ ኦቾሎ አካባቢ በዓባያ ሐይቅ ዳርቻ ላይ ተተክለዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በኦቾሎ ላንቴ ቀበሌ የቆላ ቀርከሃ ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

- Details
በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ‹‹Water Resource and Irrigation Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም ላላፉት አምስት ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ የምርምር ሥራውን ነሐሴ 26/2015 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡