
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አውስትራሊያ ሀገር ከሚገኘው ‹‹Menzies School of Health Research›› ከተሰኘ የጤና ምርምር ት/ቤት ጋር በመተባበር በሚያከናውኑት የጥናት ውጤት ላይ ግምገማዊ ወርክሾፕ መስከረም 8/2016 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የወባ በሽታ መድኃኒቶች ውጤታማነትን ለመፈተሽ እየተከናወነ የነበረው የምርምር ፕሮጀክት የጥናት ውጤት ግምገማዊ ወርክሾፕ ተካሄደ

- Details
ዕጩ ዶ/ር ከበደ ገልገሎ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በእንስሳት ሳይንስ ትምህርት ክፍል በእንስሳት ሥነ-ምግብ/Animal Nutrition/ ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ከበደ የ3ኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሑፉን የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት መስከረም 15/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናዉ ግቢ አዲሱ አዳራሽ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
Read more: የዕጩ ዶ/ር ከበደ ገልገሎ የ3ኛ ዲግሪ (PhD) መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ መርሃ ግብር

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መስከረም 10/2016 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛው መርሃ ግብር በምኅንድስና፣ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ በግብርና ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከ1,400 በላይ ተማሪዎች እንዲመረቁ አጽድቋል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ በቅድመና ድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ያሠለጠናቸውን 36ኛ ባች 2ኛ ዙር ተማሪዎች ሊያስመርቅ ነው

- Details
ዶ/ር ብሩክ አማረ ስራቴ ከአባታቸው ከአቶ አማረ ስራቴ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አልማዝ አበበ በጋሞ አውራጃ አርባ ምንጭ ከተማ መስከረም 6/1977 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምኅንድስና እና ሂሳብ (STEM) ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከማኅበረሰብ ጉድኝት ዋና ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከጋሞ፣ ጎፋ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ኮንሶ፣ ባስኬቶ፣ደራሼና አሌ ዞኖች ለተወጣጡና ከ7ኛ- 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ከነሐሴ 1-30/2015 ዓ/ም ሲሰጥ የቆየው የተግባር ተኮር ሥልጠና ጳጉሜ 1/2015 ዓ/ም ተጠናቋል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ “STEM” ማዕከል ከ7ኛ- 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የክረምት ሥልጠና ተጠናቀቀ