- Details
የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid/ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ጥቃቶች ለመከላከልና የተሞከሩ ወይም የተፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስተካከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ፖሊሲ ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ዳይሬክተሮችና ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች ከነሐሴ 19-20/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በሴፍጋርዲንግ ፖሊሲ/Safeguarding Policy/ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹International Youth Fellowship›› ከተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በአእምሮ ቀረጻ(Mind Set) ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሐምሌ 30/2014 ዓ/ም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም አቀፍ ወጣቶች ፌሎውሺፕ/ International Youth Fellowship/ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
- Details
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በካምባ፣ ገረሴ፣ ቆላ ሼሌ፣ ብርብር፣ ዋጂፎ፣ ቦዲቲና አረካ ጤና ጣቢያዎች በቡድን ሥልጠና ፕሮግራም የቆዩበትን የመስክ ሪፖርት የኮሌጁ ገምጋሚ መምህራን በተገኙበት ነሐሴ 16/2014 ዓ/ም አቅርበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የቡድን ሥልጠና ፕሮግራም /Team Training Program/ ሪፖርት አቀረቡ
- Details
በዩኒቨርሲቲው የሥልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሚተኩ አመራሮችን አወዳድሮ ለመመደብ የእጩ መልማይና የምልመላ ኮሚቴ አባላት
ነሐሴ 16/2014 ዓ/ም ተመርጠዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ተተኪ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችን ለመምረጥ የእጩ መልማይና የምልመላ ኮሚቴ ተቋቋመ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለተመረቁ ተማሪዎች ወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ በ2015 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ለ18 ተማሪዎች (AMIT 2፣ AWTI 2፣ CBE 2, CSSH 2, CMHS 2, CAS 2, CNS 2, School of Law 1, school of PBS 1, Sawula campus 2) አወዳደሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚትፈልጉ የ2014 ተመራቂ ተማሪዎች ( መስከረም 29/30 እና ሰኔ 25/26 2014 ዓ.ም የተመረቃችሁ) ከነሐሴ 18-27/2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት እንድትመዘገቡ እየገለጽን፡-
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ትምህርት ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም ለተመረቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ