የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ በአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University (AMU), College of Natural & Computational Sciences, Department of Biology, in collaboration with the Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR), hosted one-day workshop on current updates in Agribiotech and Biosafety issues on July 3, 2024. Click here to see more photos.

የ2016 ዓ/ም የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንዲፈተኑ ለተመደቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በአጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ፣ መብትና ግዴታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሐምሌ 8/2016 ዓ/ም ገለፃ /Orientation/ ተሰጥቷል፡፡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከዛሬ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University's College of Medicine and Health Sciences in collaboration with Australia's Menzies School of Health Research successfully hosted a comprehensive three day training program on Microscopic Malaria Diagnosis from July 10-12, 2024. The training convened skills of medical laboratory technicians to diverse health facilities including AMU and EPHI. Click here to see more photos.

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት መጀመሪያ ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ ስለሆነ ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም ጀምሮ በሕጻናት፣ በማኅፀንና ጽንስ፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገና እና በውስጥ ደዌ ተመላላሽ ሕክምና እንዲሁም የተለያዩ የላቦራቶሪ እና ኢሜጂንግ አገልግሎቶች አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን አገልግሎቱን በጉጉት ስትጠብቁ የነበራችሁ ሁሉ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡