የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማኅ/ጉድ/ማስ/ጽ/ቤት ለ3 አቅመ ደካማ እናቶች ነፃ የማሕፀን ውልቃት ቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት በገረሴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በኮሌጁ የማሕፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪሞችና መምህራን መጋቢት 7/2015 ዓ/ም እንዲሰጥ አድርጓል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በዓይነቱ ልዩ የሆነ ነጻ የዓይን ምርመራና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና (Cataract Surgery) አገልግሎት ከአሜሪካ በሚመጡ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የዓይን ስፔሻሊስት ሐኪሞች ጋር በመተባበር ከመጋቢት 25 - 30/2015 ዓ/ም ድረስ በሆስፒታሉ ይሰጣል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች ከመጋቢት 01-02/2015 ዓ/ም የሕይወት ክሂሎት/Life Skill/ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡