
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የተለያዩ አዳራሾች አገልግሎት የሚውል የአዳራሽ ወንበር ግዥ ሂደት ጋር ተያይዞ በተፈጠረ የጥራት/መስፈርት ልዩነት/ ችግር ምክንያት ከአቅራቢ ድርጅቱ ጋር መግባባት ባለመቻሉ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ከዚህ ቀደም በተሰጡ መግለጫዎች ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡ ጉዳዩን በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እና እንደ ኢሳትና ኢቲቪን በመሳሳሉ የግልና የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጭምር የተዛቡና አሉባልታን መሠረት ያደረጉ ዘገባዎችና የዩኒቨርሲቲውን መልካም ስምና ዝና የሚያጎድፉ መረጃዎች ሲሰራጩ መቆየታቸውም ይታወቃል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአዳራሽ ወንበር ግዥ ጉዳይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተከትሎ የተሰጠ መግለጫ
- Details
በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላ ረቡዕ ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሐሙስና ዓርብ ታኅሣሥ 3 እና 4 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ታኅሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ"Geography and Environmental Studies" ትምህርት ክፍል በ"Environment and Natural Resource Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው የዕጩ ዶ/ር ጀምበር በክረ የመመረቂያ ጽሑፍ ኅዳር 21/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ