- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 114 ሺህ ብር የሚያወጡ የሕክምና ቁሳቁሶችን ለሰላም በር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሐምሌ 14/2013 ዓ/ም ድጋፍ አድርጓል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለሰላም በር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
- Details
ሀገራችን ኢትዮጵያ በመንግሥትና በሕዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እየገነባች የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ መላው የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብና ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!!
ግድቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለሀገራችን ዕድገት መፋጠን በሙሉ አቅም አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር ለግንባታው የነበረው ሁለንተናዊ ሕዝባዊ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ማኅበረሰቡም እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀሪ የግንባታ ሥራዎች እስከሚጠናቀቁ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን አረጋግጣለሁ።
Read more: ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ከዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የተላለፈ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት በተገኙበት ሐምሌ 15/2013 ዓ/ም ተገምግሞ ጸድቋል፡፡ ከካውንስል አባላቱ በዕቅዱ ላይ ሊሻሻሉ፣ሊካተቱና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦች ቀርበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ በዩኒቨርሲቲው ካውንስል ተገምግሞ ፀደቀ
- Details
በ2013 ዓ.ም በዋናው ግቢ በቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ለተመደቡ 1,100 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በቤተ-መጻሕፍት፣ በሬጅስትራርና በተማሪዎች አገልግሎት ዘርፍ አጠቃቀም እንዲሁም በተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ ዙሪያ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ