- Details
ዩኒቨርሲቲው ለ7 ወራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የቅድመ ምረቃ ትምህርት ለማስጀመር በመማር ማስተማሩ ዘርፍ አስፋላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ ገልፀዋል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ሥራ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ
- Details
ላለፉት ሦስት ዓመታት እየጣለ ባለው ዝናብ አማካኝነት እየገባ ባለው ከፍተኛ ደለል ምክንያት የዓባያና ጫሞ ሐይቆች ከመጠን በላይ መሙላታቸውና ከብዙ ዓመታት በኋላ ሐይቆቹ ዳግም መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ ላለፉት 45 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው ጫሞ በሰገን በኩል የሚያደርገው ፍሰትም ጥቅምት 16/2013 ዓ/ም ዳግም ጀምሯል፡፡
Read more: የዓባያና ጫሞ ሐይቆች ከመጠን በላይ በመሙላት ከብዙ ዓመታት በኋላ ዳግም መገኛኘታቸው ተገለጸ
- Details
የ2013 የትምህርት ዘመን፡-
1. የምዝገባ ቀናት - ከጥቅምት 18-20/2013 ዓ.ም
2. የምዝገባ ቦታ - በካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች
3. ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ጥቅምት 23/2013 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
- Details
በ2012 ዓ/ም በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት በ2013 የትምህርት ዘመን እንዲቀጥል መንግሥት በወሰነው መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎችን ከጥቅም 25 – 26/2013 ዓ/ም የመልሶ ቅበላ መርሃ ግብር ያካሂዳል፡፡
- Details
የኤፌዴሪ ፕሬዝደንት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተገኙበት ዩኒቨርሲቲው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ቤተሰቦች የሚመጡ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት ድጋፍ እንዲያገኙ ከተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ