- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ዶርዜ ቀበሌ የቴክኒክና ሙያ እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት አጠናቀው ሥራ ላጡና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ እማወራ ሴቶች ከቀርከሃ ምርት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማምረትና መሸጥ የሚያስችል ሥልጠና ከጥቅምት 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል፡፡
Read more: ሴቶች የራሳቸዉ ገቢ እንዲኖራቸዉ የሚያስችል የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና እየተሰጠ ነው
- Details
የዩኒቨርሲቲዉ ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች መምህራን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በዋናዉ ግቢ አቅራቢያ ከሚገኙ ሦስት ቀበሌያት ለተወጣጡ 100 ተማሪዎች የመማሪያ ደብተርና እስክሪፕቶ ድጋፍ ጥቅምት 19/2013 ዓ.ም አድርጓል፡፡
- Details
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት መማር ማስተማርን ለማስቀጠል ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በቀረበው የመተዳደሪያ መመሪያ ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጥቅምት 20/2013 ዓ/ም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሥራን ለማስቀጠልና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የመተዳደሪያ መመሪያ መኖሩ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አመራር፣ መምህራን፣ አስተዳደር ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎች በግቢ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ አካላት መመሪያውን በአግባቡ ተፈፃሚ እንዲያደርጉ ዶ/ር ዳምጠው አሳስበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት በኮቪድ-19 መተዳደሪያ መመሪያ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጠ
- Details
ለአርባ ምንጭ ዩነቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ተግባቦት አማራጮች ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 25 እና 26 ግቢ እንድትገቡ ከጥቅምት 03/2013 ዓ/ም ጀምሮ ያስተዋወቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በተፈጠረው አሁናዊ አገራዊ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ አከባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር የተፈጠረ መሆኑን መገንዘብ ችለናል፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በጂኦ ስፓሻል ትምህርትና ሥልጠና፣ ምርምር፣ ዕድገት እንዲሁም መረጃ ልውውጥ ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ለዘርፉ ዕድገት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ