
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር /INSA/ ጋር በመተባበር በድሮን ካሜራ አጠቃቀም ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የትምህርትና ሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክና ከ“GIZ” ለተወጣጡ ባለሙያዎች ከሚያዝያ 3-12/2014 ዓ/ም ድረስ ለ10 ቀናት የቆየ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሺሪ ሮበርት ሼትኪንቶንግ (Shri Robert Shetkintong) በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ከሚያስተምሩ ሕንዳውያን መምህራን ጋር ሕንድ ሀገር ከሚገኙ ተቋማት ጋር በትብብር ግንኙነት በመፍጠር ምርምር፣ ማኅበረሰብ አገልግሎትና የቴክሎጂና የፈጠራ ሥራዎችን በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሚያዝያ 12/2014 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል በኢንፎማይንድ ሶሉሽንስ ንዑስ የቢዝነስ ዩኒት ከሆነው ደረጃ ዶት ኮም ኃ.የተ.የግ. ድርጅት /Dereja.Com/ ጋር በመተባበር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በ2014 ዓ/ም ለሚመረቁ ተማሪዎች ከሚያዝያ 4-7/2014 ዓ/ም የተቀጣሪነት ክሂሎት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
- Details
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ በ2014 የትምህርት ዘመን ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ፡-