
- Details
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር 28ኛው ሀገር አቀፍ ኮንፍራንስ ላይ ከቀረቡ ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶች ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቅ ሀና እንዳሻውና በማስተርስ ዲግሪ ምሩቅ ሁሴን አሊ የላቀ የመመረቂያ ጽሑፍ በማቅረብ ታኅሣሥ 9/2014 ዓ/ም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
Read more: በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ኮንፍራንስ 2 የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን በላቀ የመመረቂያ ጽሑፍ ተሸላሚ ሆኑ

- Details
በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኤሌትሪካል እና ኮምፕዩተር ምኅንድስና ፋከልቲ መምህር፣ ተመራማሪና አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አንቺት ቢጀልዋን (Dr Anchit Bijalwan) ‹‹Network Forensics፡ Privacy and Security›› በሚል ርዕስ 2ኛ መጽሐፋቸውን አሳትመዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ዶ/ር አንቺት ቢጀልዋን ‹‹Network Forensics፡ Privacy and Security›› በሚል ርዕስ 2ኛ መጽሐፋቸውን አሳተሙ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ2013 ዓ/ም የሥራ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና የካውንስል አባላት ጋር ከታኅሣሥ 7-9/2014 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና የካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በፎረንሲክ ወንጀል ምርመራ ዘዴና ማስረጃ አያያዝ ዙሪያ ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ 36 የፎረንሲክ ምርመራ ፖሊስ መኮንኖች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ለተወጣጡ የጥበቃ ሠራተኞች ከታኅሣሥ 7-9/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የ2014 ዓ/ም የ1ኛ ተርም የአዲስ ተመዝጋቢዎች የ1ኛ ሴሚስተር የርቀት ትምህርት የምዝገባ፣ የቲቶሪያልና የፈተና መርሃ-ግብር ከዚህ ቀጥሎ ባለው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በተመዘገባችሁበት ማዕከል የሚከናወን መሆኑን እየገለጽን በጊዜ ሠሌዳዉ መመዝገብ ያልቻለ ተማሪ በቅጣት መመዝገብ የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡