- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል በማቴሪያል ፊዚክስ የዶክትሬት ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የውጭ ሥርዓተ ትምህርት ነሐሴ 18/2012 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል፡፡
የአካዳሚክ ጉ/ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ትውልድና የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ የ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን በማስፋፋትና በጥራት መስጠት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሠራ የቆየ ሲሆን በፊዚክስ ትምህርት መስክ የሚከፈተው የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራምም የዚሁ ሥራ አካል ነው ብለዋል፡፡ አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች ሲከፈቱ የሥርዓተ-ትምህርቱ ዝግጅት በርካታ ሂደቶችን እንደሚያልፍ የገለፁት ዶ/ር የቻለ ፕሮግራሞችን መክፈት በራሱ ግብ ባለመሆኑ ሥርዓተ-ትምህርቱን በየጊዜው የመከለስ እንዲሁም ትምህርቱን በጥራት መስጠትና ምርምር ተኮር የማድረግ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ በቀጣይነት ይሠራል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማቴሪያል ፊዚክስ የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሊከፍት ነው
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ የሚገኘውን የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታን በ2013 በጀት ዓመት በከፊል ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደት ነሐሴ 15/2012 ዓ/ም በጎበኙበት ወቅት ተገልጿል፡፡
በ2007 ዓ/ም የተጀመረው የሆስፒታሉ ግንባታ በዲዛይን ማስተካከያና ተጨማሪ ግንባታ፣ በሆስፒታሉ ግንባታ ቦታ ተነሺዎች፣ የክፍያዎች መዘገየት፣ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት፣ በግንባታ አካባቢ የሚገኙ የመብራት፣ የውሃና የስልክ መስመሮች እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ የዘገየ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት 77 በመቶ የግንባታ ሂደት መጠናቀቁ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ የሚገኘውን የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዞችን ሐምሌ 20/2012 ዓ/ም ጉብኝተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን ጉብኝቱ በዩኒቨርሲቲው ያሉ የተለያዩ የገቢ ማመንጫ ተቋማት ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃና ችግሮች በአካል በማየት ለቀጣይ ሥራዎች አቅጣጫና ውሳኔ ለመስጠት የሚረዱ ሀሳቦች ለማግኘት የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ገቢ በማመንጨት ወጪያቸውን በከፊል እንዲሸፍኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በ2007 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የእንጨትና ብረታ ብረት፣ የሕትመትና የግብርና ኢንተርፕራይዞች ተመስርተው ሲሰሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት ም/ፕሬዝደንቷ መሰል ጉብኝቶች መደረጋቸው የዘርፉን ወጤታማነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው ብለዋል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች የዩኒቨርሲቲውን የገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኙ
- Details
A Philippine expatriate, Dr Eliezer B Manus, 65, who worked with Arba Minch University for over 13 years in Architecture & Urban Planning Department, died of prolonged illness, was buried in Manila, Philippine. He is survived by wife Prof Madelyn Manus and only son Mr Michael Manus, a lecturer in AMU.
Dr Eliezer had started his employment with AMU on 9th October, 2007, till he left for his country in August 2020 for treatment to his ailment and soon after reaching his nation he died. Click here to see the pictures
Read more: Dr Eliezer Manus: Kindness and humility personified
- Details
The Ethiopian Journal of Water Science and Technology (EJWST) is an open access journal hosted by Arba Minch University, Water Technology Institute. EJWST is a multidisciplinary double-blind peer-reviewed journal publishes original research papers, critical reviews and technical notes which are of regional and international significance on all aspects of the water science, technology, policy, regulation, social, economic aspects, management and applications of sustainable of water to cope with water scarcity.