- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ እና የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በማዘጋጀት ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ ለኢንተርን ሐኪሞችና ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች እያሰራጩ መሆናቸውን ገለፁ፡፡ኮሌጆቹ ምርቱን በብዛት በማምረት ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጭምር የማዳረስ ዕቅድ እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡
በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የባዮ-ቴክኖሎጂ መምህርና ተመራማሪ አቶ አዲሱ ፈቃዱ እንደገለፁት የንጽህና መጠበቂያው የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት የተዘጋጀ ሲሆን ምርቱም በዋናነት አልኮል፣ ግሊሲሮልና ሃይድሮጅን ፔርኦክሳይድ የተባሉ ንጥረ-ነገሮችን በመጠቀም የሚዘጋጅ ነው ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት ይህንን ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ እና የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በማዘጋጀት እያሰራጩ ነው
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤኔፊት ሪያላይዝ (BENEFIT-REALISE) ፕሮግራም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማስጠበቅና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በአርባ ምንጭ ክላስተር በምዕራብ አባያ፣ ደራሼ፣ ዛላና ቁጫ ወረዳዎች በሚገኙ 16 ቀበሌያት ምርጥ ዘሮችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የፕሮግራሙ አስተባባሪ ዶ/ር መብራቱ ዓለሙ እንደገለጹት የፕሮጀክቱ ዓላማ መልካም ተሞክሮዎችንና የተለያዩ ዝርያዎችን ከምርምር ጣቢያዎች በማምጣት የሴፍቲኔት ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት ይህንን ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤኔፊት ሪያላይዝ (BENEFIT-REALISE) ፕሮግራም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማስጠበቅ እየሠራ ይገኛል
- Details
AMU’s Water Technology Institute has signed 2-year joint project as part of the university cooperation for development of Flemish Interuniversity Council (VLIR) called, JOINT Project 2020 ‘Internet of Drops: Linking small water-related observations towards a cloud of data with IoT-enabled sensor networks’ with KU Leuven, Ecuador’s National Polytechnic School and Catholic University of Cuenca which is funded by VLIRUOS. Click here to see the pictures
Read more: AWTI with global partners bag ‘JOINT Project 2020’
- Details
The first ever talk-show on Ethiopia’s hydropower giant - Grand Ethiopian Renaissance Dam hosted by Walta TV at Haile Resort, Arba Minch has mirrored the deep-rooted anguish, seething anger and concern of professionals, academicians of AMU community, who unanimously stand for its completion.
Professionals from Water Resources Engineering, Law, Academics, Research & Community Service countering Egypt’s argument on Nile River espoused ongoing public and diplomatic engagements by Ethiopian government and at different forums will establish Ethiopian standpoint in stronger manner. Click here to see the pictures
Read more: GERD: AMU collectively trashes Egypt’s argument as hollow
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሳሀይ ሶላር ፕሮጀክት አማካይነት በጨንቻ ወረዳ የሚገኘውን ጉልታ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከየካቲት 20/2012 ዓ/ም ጀምሮ የ24 ሰዓት የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሳሃይ ሶላር ፕሮጀክት ጉልታ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤትን የ24 ሰዓት የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ አደረገ