
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አውስትራሊያ ሀገር ከሚገኘው ‹‹Menzies School of Health Research›› ከተሰኘ የጤና ምርምር ት/ቤት ጋር ‹‹Effectiveness of Novel Approaches to Radical Cure of Vivax Malaria with Tafenoquine and Primaquine›› በሚል ርዕስ የሚያከናውኑትን ግራንድ የምርምር ፕሮጀክት መጀመር የሚያስችል በ‹‹Clinical Trial›› የምርምር ሥነ-ምግባርና ፕሮቶኮሎች ዙሪያ በምርምሩ ለሚሳተፉ ስፔሻሊስት ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ከት/ቤቱ በመጡ ባለሙያ ከጥር 13/2014 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የወባ በሽታ መድኃኒቶች ውጤታማነትን ለመፈተሽ የሚከናወነውን የምርምር ፕሮጀክት ለመጀመር ሥልጠና ተሰጠ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ላላፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እጩ ዶ/ር እንደልቡ ጎኣ የምርምር ሥራቸውን ጥር 14/2014 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የዩኒቨርሲቲው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
መልካም በዓል!!

- Details
የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በኃላፊነት ላይ ላሉ ሴት መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የአመራርና የአስተዳደር ክሂሎት እንዲሁም ለጸሐፊዎችና የቢሮ ረዳቶች በሥርዓተ ጾታ፣ ጾታዊ ትንኮሳና ጥቃትን በመከላከል ላይ ከጥር 04 - 06/2014 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በሥርዓተ ጾታ፣ ጾታዊ ትንኮሳና ጥቃትን በመከላከል ላይ እንዲሁም የአመራርና የአስተዳደር ክሂሎት ሥልጠና ተሰጠ::

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት፣ ሶፍትዌር፣ የዌብ ጂ.አይ.ኤስ (GIS)ና የጂኦዳታቤዝ አስተዳደር መተግበሪያዎች አቅራቢ ድርጅት ከሆነው ‹‹Environmental Systems Research Institute (ESRI)›› ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለመማር ማስተማር፣ ለምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራና አስተዳደራዊ ሥራዎች የሚውል ‹‹ArcGIS›› ሶፍትዌርን ለ3 ዓመታት በነፃ የመጠቀም ፈቃድ አግኝቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹ArcGIS›› ሶፍትዌርን ለ3 ዓመታት በነፃ የመጠቀም ፈቃድ አገኘ