- Details
የ2014 ዓ/ም የ1ኛ ተርም የአዲስ ተመዝጋቢዎች የ1ኛ ሴሚስተር የርቀት ትምህርት የምዝገባ፣ የቲቶሪያልና የፈተና መርሃ-ግብር ከዚህ ቀጥሎ ባለው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በተመዘገባችሁበት ማዕከል የሚከናወን መሆኑን እየገለጽን በጊዜ ሠሌዳዉ መመዝገብ ያልቻለ ተማሪ በቅጣት መመዝገብ የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባዮ ቴክኖሎጂ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አዲሱ ፈቃዱ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በተደረገ ሀገር አቀፍ የምግብ ፈጠራ ሥራዎች ውድድር 1ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ውድድሩ ከኅዳር 29 - ታኅሣሥ 1/2014 ዓ/ም ከተካሄደው ሀገር አቀፍ የሥነ-ምግብ ምርምር ኮንፍረንስ ጋር ተያይዞ የተደረገ ሲሆን በውድድሩ ከ11 ተቋማት የተወጣጡ የፈጠራ ሰዎች ተካፍለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ዶ/ር አዲሱ ፈቃዱ በሀገር አቀፍ የምግብ ፈጠራ ሥራዎች ውድድር 1ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኑ

- Details
የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ አማርኛ ት/ክፍል ጋር በመተባበር ለአርባ ምንጭ ከተማ ማረሚያ ተቋም፣ ለጨንቻ ከተማ ወጣቶች ቤተ-መጻሕፍትና በጨንቻ ለሚገኘው ሆሎኦና ላካ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ታኅሣሥ 6/2014 ዓ.ም የመጻሕፍት ድጋፍ አድርጓል፡፡ መጻሕፍቱ በቁጥር 433 ሲሆኑ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ የተለያዩ ጀግኖች ታሪክ፣ ልብወለዶች፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ፣ የቋንቋ እና የትምህርት ማጣቀሻዎችን የሚያካትቱ ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ት/ክፍል ከዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት እና ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስትሮኖሚና አስትሮ ፊዚክስ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ታኅሣሥ 04/2014 ዓ/ም ሥልጠናዊ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ በወርክሾፑ ማጠናቀቂያም በኢንስቲትዩቱ እንደ ሀገር ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በጉጌ ተራራ በመገኘት የጣቢያ ምልከታ ተከናውኗል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአስትሮኖሚ ጣቢያዎች /Astronomical sites/ ላይ ወርክሾፕ እና የጉጌ ህዋ ሳይንስ ጣቢያ ምልከታ ተካሄደ

- Details
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን፣ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የዘማች ቤተሰቦችን ለመደገፍ የ2ኛ ደረጃ መምህራንንና ተማሪዎችን በማሳተፍ የተጀመረው ሀገራዊ የድጋፍ ዘመቻ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዩኒቨርሲቲው ኮሚዩኒቲ ት/ቤት ታኅሣሥ 01/2014 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካሄደ