- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል ላለፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እጩ ዶ/ር መኮንን ሬዲ የካቲት 11/2014 ዓ/ም የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች በተገኙበት የምርምር ሥራቸውን አቅርበዋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የዩኒቨርሲቲው የስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት ለ2014 ዓ/ም አዲስ ተቀጣሪ መምህራን ከየካቲት 7-11/2014 ዓ/ም መሠረታዊ የማስተማር ሥነ-ዘዴ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
ሥልጠናው የትምህርት ዕቅድ አዘገጃጀት፣ የክፍል ውስጥ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀም፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሥነ-ምግባር ሕጎች፣ የክፍል አያያዝና ቁጥጥር፣ የትምህርት ምዘናና ተማሪ ተኮር የማስተማሪያ ሥነ-ዘዴ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የሳሃይ ሶላር ፕሮጀክት የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የካቲት 14/2013 ዓ/ም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ፕሮጀክቱ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ በቀደሞው ጋሞ ጎፋ ዞን፣ በUniversity of Applied Sciences and Arts of Southern Switzerland እና በሳሃይ ሶላር ማኅበር እ.ኤ.አ በ2015 በተፈረመ የትብብር ስምምነት መሠረት የተከናወነ ሲሆን በእስከ አሁን ቆይታው 23 ጤና ጣቢያዎችንና 6 ት/ቤቶችን የ24 ሰዓት የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉ በዳሰሳ ጥናቱ ተመልክቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ሳሃይ ሶላር ፕሮጀክት በእስከ አሁን ቆይታው 23 ጤና ጣቢያዎችንና 6 ት/ቤቶችን የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉ ተገለጸ
- Details
የዩኒቨርሲቲው ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣ ከለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና ከማኔጅመንት ት/ክፍል ጋር በመተባበር ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች በደንበኛ አያያዝና ጥራት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከየካቲት 10-11/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት በነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሥራ አፈፃፀምና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ከነፃ የሕግ ድጋፍ ማዕከላት አስተባባሪዎችና ከት/ቤቱ መምህራን ጋር የካቲት 12/2014 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሥራ አፈፃፀምና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
- የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ /INSA/ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር መሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ
- የ2014 ዓ/ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ተገመገመ
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአርባ ምንጭ ከተማ ከሚገኙ ት/ቤቶች ለተወጣጡ የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምኅንድስናና ሒሳብ ትምህርት መስኮች የተግባር ሥልጠና እየሰጠ ነው
- በፍትሕና የሕግ አገልግሎት ሥራዎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የእውቅናና የዋንጫ ሽልማት ተበረከተለት