- Details
ተማሪ ጽጌሬዳ ግርማይ ከአባቷ ከአቶ ግርማይ ገ/መድኅን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ያበሻ ያዘዘው ወልቃይት ወረዳ አዲ ረመጽ ከተማ በ1993 ዓ/ም ተወለደች፡፡
ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ የመሰናዶ ትምህርቷን በወልቃይት ጌታቸው አዘናው 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትላለች፡፡ ፎቶዎችን ለማየት
- Details
በዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከ13 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለተወጣጡ መምህራን ‹‹Solid work››፣ ‹‹Arc cad›› እና ‹‹Auto cad›› በተሰኙ የኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከጥር 16-20/2014 ዓ/ም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
- Details
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴርና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ‹‹ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት ም/ፕሬዝደንት፣ ዳይሬክተሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ጥር 21/2014 ዓ/ም ውይይት አካሂደዋል፡፡
Read more: ‹‹ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም እንገንባ ›› በሚል መሪ ቃል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውይይት ተካሄደ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አውስትራሊያ ሀገር ከሚገኘው ‹‹Menzies School of Health Research›› ከተሰኘ የጤና ምርምር ት/ቤት ጋር ‹‹Effectiveness of Novel Approaches to Radical Cure of Vivax Malaria with Tafenoquine and Primaquine›› በሚል ርዕስ የሚያከናውኑትን ግራንድ የምርምር ፕሮጀክት መጀመር የሚያስችል በ‹‹Clinical Trial›› የምርምር ሥነ-ምግባርና ፕሮቶኮሎች ዙሪያ በምርምሩ ለሚሳተፉ ስፔሻሊስት ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ከት/ቤቱ በመጡ ባለሙያ ከጥር 13/2014 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የወባ በሽታ መድኃኒቶች ውጤታማነትን ለመፈተሽ የሚከናወነውን የምርምር ፕሮጀክት ለመጀመር ሥልጠና ተሰጠ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ላላፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እጩ ዶ/ር እንደልቡ ጎኣ የምርምር ሥራቸውን ጥር 14/2014 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡