
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከሮማንና ኃይለማርያም ፋውንዴሽን፣ ከቤልጂየሙ ኬዩሊዩቨን ዩኒቨርሲቲ/KU Leuven University/ እና ቢኦኤስ+/BOS+/ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር በጫሞ ሐይቅ ተፋሰስና ረግረጋማ ቦታዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የተጀመረው የሙከራ /Pilot/ ፕሮጀክት አፈፃፀም ውጤታማና ለቀጣይ ሰፋፊ ሥራዎች ማሳያ ልምዶች እየተገኙበት መሆኑ ተገለጸ፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የጫሞ ሐይቅ ተፋሰስ ረግረጋማ ቦታዎችን መልሶ ለማልማት የተጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በደንበኛ አያያዝ፣ ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም አመራርነት ክሂሎት ዙሪያ ከ5ቱም ካምፓሶች ለተወጣጡ ሴት መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና አመራሮች ከየካቲት 9-10/2015 ዓ/ም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአሜሪካው ቴክሳስ ግብርናና ሜካኒካል ዩኒቨርሲቲ/ Texsas Agricultural & Mechanical University/ ጋር በመተባባር ‹‹Integrated Decision Support System (IDSS)›› በሚል ርዕስ ከጎረቤት ሀገራት ለመጡና ከሀገር ውስጥ ለተወጣጡ በውኃ ምኅንድስና፣ ግብርና፣ ኢኮኖሚክስ፣ አካባቢ ጥበቃና ሌሎች ዘርፎች የሚያስተምሩ መምህራንና ባለሙያዎች ከጥር 6-10/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ‹‹Integrated Decision Support System›› በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ከሳሃይ ሶላር አሶሴሽን/Sahay Solar Association/ ጋር በመተባበር ከስዊዘርላንድ፣ ከጋሞና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ለተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተማሪዎች የፀሐይ ኃይልን ለመብራትና ለተለያየ አገልግሎት መጠቀም በሚያስችሉ ዘዴዎች /Photovoltaic Technology/ ዙሪያ ከጥር 30 - የካቲት 9/2015 ዓ/ም ለተከታታይ 9 ቀናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡