- Details
አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ጋር በመተባበር “አርባ ምንጭ ታንብብ!” በሚል መሪ ቃል ታላቅ የንባብ ሳምንት አዘጋጅቷል፡፡ የንባብ ሳምንቱ በአርባ ምንጭ ከተማ ከጥር 18-21/2016 ዓ/ም ማለትም ከፊታችን ዓርብ እስከ ማክሰኞ ድረስ ድግሱ ለአራት ቀናት ይቆያል፤ ድንቅ መርሃ ግብሮች ተካተውበታል፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የዩኒቨርሲቲው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
መልካም በዓል!!
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኔዘርላንድ ሀገር ከሚገኝ “KNCV Tuberculosis Foundation” ከተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በምርምርና መማር ማስተማር ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ጥር 7/2016 ዓ/ም ተፈራርሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
የኢትዮጵያ ሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በየዓመቱ ብሩህ ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ያካሂዳል፡፡ በዚህ ውድድር አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ በማሸነፍ ከግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ይሰለፋል፡፡ በተመሳሳይ በ2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የብሩህ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ሃሳብ ውድደር ተማሪዎችን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ሥልጠና በማሰልጠንና በማወዳደር የተሻለ ሃሳብ ያላቸውን ተማሪዎች ለብሩህ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የምንልክ መሆኑን እየገለፅን በዚህ ውድድርና ሥልጠና የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ በአንክሮ እናሳስባለን፡፡ ምዝገባው የሚካሄደው ከጥር 10 - 17/2016 ዓ.ም ሲሆን የቢዝነስ ሃሳብ ተወዳዳሪዎች በግል ወይም በቡድን መወዳደር ይችላሉ፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቀድሞው የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ባደረገው የማዕድን አለኝታ ጥናት በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ከ950 ሚሊየን ቶን በላይ የብረት እንዲሁም 429 ሚሊየን ቶን የድንጋይ ከሰል ማዕድን ከምችት መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ከ950 ሚሊየን ቶን በላይ የብረት ማዕድን ከምችት መኖሩ በጥናት ተረጋገጠ
- የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሥርዓተ-ትምህርቶች ውስጥ የተካተቱ ተግባራትና ስታንዳርዶች በአግባቡ መተግበራቸውን ለመቆጣጠር የሚያስችል ፕላትፎርም በማበልጸግ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ እያደረገ ነው
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአርባ ምንጭ ከተማ ላይ በ17.2 ሚሊየን ብር ያስገነባውን አደባባይ በ8ኛው የማኅበረሰብ ጉድኝት ቀን አስመረቀ
- 8ኛው ዙር የማኅበረሰብ ጉድኝት ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
- በቪዲዮ የተመሠረተ የጤና ትምህርት በእናቶችና ጨቅላ ሕፃናት ጤና ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በጥናት ተገለጸ