- Details
የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት የባህሪ ማሻሻያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ “International Youth Fellowship” ጋር በመተባበር በአዕምሮ ውቅር (mindset) ዙሪያ ከኮሪያ በመጡ አሠልጣኞች ለጫሞ፣ ለዋናው ግቢ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው መደበኛ፣ ኢ-መደበኛና ለሁሉም ሪሚዲያል ተማሪዎች፣ ለባይራ አዳሪ 2ኛ ደ/ት/ቤት ተማሪዎች እና ለአርባ ምንጭ ከተማ መምህራን ከጥር 17-18/2016 ዓ.ም በዋናው ግቢ በሚገኝ አዳራሽ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሁሉ አቀፍ ሴክተር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከአርባ ምንጭ ከተማና ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ለመጡ ወጣቶች እና ለስፖርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች በሰብእና ግንባታ (Mindset) ዙሪያ ከጥር 06-09/2016 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ከአርባ ምንጭ ከተማና ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ለተወጣጡ ወጣቶች በሰብእና ግንባታ ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
Arba Minch Institute of Technology (AMiT) in Arba Minch University in collaboration with DAAD Information Center in Ethiopia held a presentation program on free scholarship opportunities in Germany.Click here to see more photos.
- Details
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓባያ ካምፓስ የ2016 ዓ/ም 1ኛ ዓመት ሴት ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበልና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ነባር ሴት ተማሪዎች የሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብር ጥር 08/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡
ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለዓባያ ካምፓስ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበል ተካሄደ
- Details
ረ/ፕ ታደሰ አብርሃም ከአባታቸው ከአቶ አብርሃም ወርቁ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዴ ተሰማ በቀድሞው ወሎ ክፍለ ሀገር በደሴ ዙሪያ ወረዳ መስከረም 3/1953 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ረ/ፕ ታደሰ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅግጅጋ እና በአፊሲን እንዲሁም የመለስተኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጋምቤላ፣ ጐሬና ባዕደማርያም ላቦራቶሪ ት/ቤቶች ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡