
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ"Geography and Environmental Studies" ትምህርት ክፍል በ"Environment and Natural Resource Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው የዕጩ ዶ/ር ወርቅአፈራሁ አመነሸዋ የመመረቂያ ጽሑፍ ዛሬ ታኅሣሥ 05/2017 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ አንጋፋና ገናና ስም ያለው በሀገራችን ከሚገኙ የመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ እንዲሆን ለማስቻል መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሚና ወሳኝ ድርሻ አለው ብለን እናምናለን፡፡
Read more: ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት አዲስ ለተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠ የመልካም ምኞት መግለጫ

- Details
ዶ/ር ኢንጂነር ቦጋለ ገብረማርያም በ1981 የመጀመሪያ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Civil Engineering››፣ በ1986 ዓ/ም ድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ (Post Graduate Diploma) በ‹‹Hydraulic Engineering (Hydro informatics)›› ኔዘርላድ ሀገር ከሚገኘው ‹‹International Institute for Infrastructural, Hydraulic and Environmental engineering (IHE), Delft››፣ በ1987 ዓ/ም ከዚሁ ተቋም በ‹‹Hydraulic Engineering (Hydro informatics)›› የማስተርስ ዲግሪ፣ በ2000 ዓ/ም ጀርመን ከሚገኝ ‹‹Freie University of Berlin›› በ‹‹Lake Hydrodynamics›› የትምህርት ዘርፍ የሦስተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
Read more: ዶ/ር ኢንጂነር ቦጋለ ገብረማርያም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ተወካይ