- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሒሳብ ት/ክፍል በ‹‹Numerical Analysis›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ወንድምአገኘሁ ስምዖን የካቲት 26/2016 ዓ/ም የምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የልማታዊ ቡድን ሥልጠና ፕሮግራም (DTTP) በአርባ ምንጭ ከተማ ውስጥ በመናኸሪያ ግቢ የተከናወኑ የንጹሕ መጠጥ ውኃ መስመር ዝርጋታና የመንገደኞች ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲሁም በሴቻ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግቢ የተገነባው አነስተኛ ለHIV/AIDS ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የቅድመ መከላከያና ማማከሪያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የካቲት 23/2016 ዓ/ም ለማኅበረሰቡ የማስተላለፍ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በልማታዊ ቡድን ሥልጠና ፕሮግራም (DTTP) የተከናወኑ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን ለማኅበረሰቡ የማስተላለፍ መርሃ ግብር ተካሄደ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎክን የመጻሕፍትና መረጃ ማዕከል የብዕር ጥበብ በተሰኘ ዓመታዊ የሥነ ጽሑፍ ቀን የተለያዩ ደራሲያንና ገጣሚያን በተገኙበት የካቲት 24/2016 ዓ/ም በተለያዩ ሥነ ጽሑፎች፣ ተውኔቶች፣ ወጎችና መነባንቦች የዐድዋን ድል ዘክሯል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የዐድዋ ድልን በማስመልከት 2ኛው ዓመታዊ የብዕር ጥበብ መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲው ተካሄደ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ‹‹ዝክረ ዐድዋ ድል ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ሰላም›› በሚል ርእስ 128ኛውን የዐድዋ ድል በዓል የካቲት 23/2016 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አክብሯል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት፣ አሜሪካ ሀገር የሚገኘው አላባስተር ኢንተርናሽናል/Alabaster International እንዲሁም ኬንያ የሚገኙት ገርል ቻይልድ ኔትወርክ/ Girl Child Network እና ጆሞ ኬንያታ የግብርናና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ/ Jomo Kenyatta University of Agriculture and Technology በመተባበር ‹‹Enset Cultivation, Development and Utilization in Ethiopia and Kenya›› በሚል ርእስ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው የጀመሩት ዓለም አቀፍ የምርምር ትብብር ፕሮጀክት እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ እ.ኤ.አ. ጥር 01, 2023 ተጀምሮ ለሦስት ዓመታት የሚቆየው ፕሮጀክት ከአንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ በጀት የተመደበለት ሲሆን በዋናነት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና በ‹‹Jomo Kenyatta University of Agriculture and Technology›› የሚተገበርና በ‹‹Alabaster International›› እና ‹‹Girl Child Network›› በገንዘብ የሚደገፍ ነው፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: እንሰትን የምሥራቅ አፍሪካ የምግብ ዋስትና መፍትሔ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ ነው