- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በምርምር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ የኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች ከጥር 23 - 26 ለአራት ተከታታይ ቀናት የጂአይኤስ አጠቃቀም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና ተመራማሪዎች በጂአይኤስ/GIS/ ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣንና ከጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር “የጋሞ ዱቡሻ እና የዱቡሻ ዎጋ˝ ሥርዓት የጥናትና ምርምር ማስጀመሪያ የማኅበረሰብ ንቅናቄ መድረክ ጥር 25/20/16 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: “የጋሞ ዱቡሻ እና የዱቡሻ ዎጋ" የጥናትና ምርምር ማስጀመሪያ የማኅበረሰብ ንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት የአምሳለ ፍርድ ቤት ፍጻሜ ውድድር ጥር 23/2016 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ውድድር ኢትዮጵያንና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን በመወከል በታንዛንያ አሩሻ በተደረገው ጠቅላላ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውድድር ተሳትፈው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የፎረንሲክ ሜዲስንና ቶክሲኮሎጂ ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ከታኅሣሥ 18 - ጥር 24/2016 ዓ/ም በሁለት ዙሮች የፎረንሲክ ናሙና ምርመራ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለፎረንሲክ ሜዲስንና ቶክሲኮሎጂ ስፔሻሊቲ ተማሪዎች የፎረንሲክ ናሙና ምርመራ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በኢኮኖሚክስ ት/ክፍል በ“Development Economics” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ የካቲት 01/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ መግቢያ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ያቀርባል፡፡