አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ትኩረት የሚሹ ቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ከኒዮርክ እና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ የቆዳ ስር ፈንገስ/Mycetoma/ በሽታ ጫናና ስርጭትን ለማወቅ የሚያስችል የምርምር ፕሮጀክት ሰኔ 24/2016 ዓ/ም ይፋ አድርጓል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ግዙፍ የማስተማሪያ፣ የምርምር እንዲሁም የሕክምና ማዕከል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቅድመና ድኅረ ምረቃ መርሃ ግብሮች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 2,544 ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በመደበኛና በሳምንት መጨረሻ ያስተማራቸውን 338 የመጀመሪያና የ2 ዲግሪ ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ለ7 ጊዜ አስመርቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በቅርቡ ተመርቆ ሥራ በሚጀምረው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሰኔ 23-24/2016 ዓ/ም የጽዳት ዘመቻና የምድረ ግቢ ማስዋብ ሥራ ተካሂዷል።

በሥራው ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ሠራተኞችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡