የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕርነርሽፕ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት  ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኢንተርፕርነርሽፕ ሥልጠና በ25/06/2015 ዓ/ም አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም በግቢ ቆይታችሁ ከዚህ በፊት የኢንተርፕርነርሽፕ ሥልጠና ያልወሰዳችሁ ብቻ እና ለመውሰድ ፍላጎቱ ያላችሁ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከ2፡30 ጀምሮ በመገኘት ሥልጠናውን እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡

የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ለተማሪዎች መኝታ አገልግሎት ተቆጣጣሪዎች በስነ-ምግባር ደንብና በሙስና ወንጀል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የካቲት 16/2015 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአራቱም ፋከልቲዎች ለተወጣጡ 19 መምህራን ‹‹Basic Python for Environmental Data Processing›› በሚል ርዕስ ከየካቲት 4-14/2015 ዓ/ም 2 ዙር የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡