አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን በተሰጠው ግብረ መልስና ሌሎች ተያያዥ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመኅበረሰቡ ውይይት እያካሄደ ይገኛል
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን ለዩኒቨርሲቲው በሰጠው ግብረ መልስና ሌሎች ተያያዥ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ከታኅሣሥ 04-11/2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም ካምፓሶች ከአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራን ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
በኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አማካኝነት የስፓኒሽ ኤጀንሲ “Agency for International Development Cooperation/AECID” ለዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ 16 ኮምፒውተሮች ከነወንበርና ጠረጴዛቸው፣ አንድ የቀለም ፕሪንተር፣ አንድ የፎቶኮፒ ማሽን፣ አንድ ፕሮጀክተር፣ ሦስት የዋይፋይ ራውተርና ሌሎች አጋዥ ግብዓቶችን ኅዳር 28/2016 ዓ/ም አበርክቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል የኮምፒውተር ድጋፍ ተበረከተ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋምና ከምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ‹‹Female Presence in Research and Grant writing›› በሚል ርእስ ለዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን በምርምርና ግራንት አጻጻፍ ዙሪያ ከታኅሣሥ 01-04/2016 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታልና ‹‹Hope of Light›› የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተቋርጦ የነበረውን የማሕጸን ፌስቱላ ሕክምና ዳግም ለማስጀመር የሚያስችልና ለ10 ዓመታት የሚቆይ የመግባቢያ ስምምነት ታኅሣሥ 02/2016 ዓ/ም ተፈራርመዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የማሕጸን ፌስቱላ ሕክምናን ዳግም ለመጀመር የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ
- Details
‹‹Human Bridge›› የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ታኅሣሥ 01/2016 ዓ/ም የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ