- Details
በዩኒቨርሲቲው የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በዓለም አቀፍ ደረጃ 20ኛውና በኢትዮጵያ 19ኛው የፀረ ሙስና ንቅናቄ ቀን ‹‹ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በኅብረት እንታገል›› በሚል መሪ ቃል ኅዳር 25/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: 20ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ንቅናቄ ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
- Details
Arba Minch University English Language Improvement Center, ELIC, along-with English Language Fellows of the US State Department organized 2-day training on Academic and Grant Writing, Scholarly Databases, and Publication for over 100 staff members from Nov 30 to Dec 1, 2023. Click here to see more photos.
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞንና ወረዳዎች ለተወጣጡ ከፍተኛ መኮንኖችና የዲቪዥን ኃላፊ ሴት አመራሮች የአመራርነት ሚናን ለማጎልበት ከኅዳር 19-20/2016 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው የአመራር ምንነት፣ የጥሩ መሪ መገለጫ ባህሪያት እንዲሁም ራስን፣ ቡድንና ተቋምን መምራት የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከጋሞ ዞን ለተወጣጡ ከፍተኛ መኮንኖችና የዲቪዥን ኃላፊ ሴት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ጽ/ቤት እና ከምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ኅዳር 20/2016 ዓ/ም በዶርዜ ሆሎኦና ላካ ቀበሌ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል እንዲሁም በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚገኙ የቢራ ገብስ ዝርያዎች የመስክ ምልከታና የዝርያ መረጣ አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል እና በአርሶ አደር ማሳ ላይ የሚገኙ የቢራ ገብስ ዝርያዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ
- Details
በ2015 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት በማምጣት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2015 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ታኅሣሥ 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡